Friday, September 21, 2012

በየቤቱ የታደለ የፍቅር ደብዳቤ


በየቤቱ የታደለ የፍቅር ደብዳቤ
    በግሩም ተ/ሀይማኖት
 በጥበብ እና በፍቅር ዙሪያ አንዳንድ ትዝብቶችን ለማስነበብ አስቤ ነው ይህን ለመጻፍ የተነሳሳሁት፡፡ ይህ ብሎግ የተዘጋጀውም በዚህ ዙሪያ ያሉ መልዕክቶችን ለማስፈሪያ ነው እና ገጠመኛችሁን ላኩልኝ፡፡ የየጊዜው ጽሁፎች ቀጥታ እንዲደርስዎ ከፈለጉ ጆይን ዚስ ዌብ የሚለው ላይ ኤሜል አድራሻዎትን ይሙሉ፡፡

    ፍቅር የሚለውን ቃል ታፔላ አድርገው እኩይ ሽምቅ ውጊያ የሚከፍቱ አሉ፡፡ ይቺንም ያችንም ማተራመስ እርድና የሚመስላቸው ሞልተዋል፡፡ ለፍቅር ስለፍቅር ሲሉ የተሰደዱም ገጥመውጣል፡፡ እዚህ የመን ውስጥ ሰሞኑን የገጠመኝን ገጠመኝ ላውጋዎት፡፡ አንድ እንደ እህቴ የምቀርባት ህሊና የምትባል ልጅ የሆነ ቦታ ስትጓዝ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ትገናኛለች፡፡ ልጁ በፈጣን ተናጋሪነቱ ይታወቃል፡፡ ስትነግረኝ ምን ያድረግ ለቃላቶቹ አይከፍልባቸው ዝም ብሎ ሲያወራ ዋለ ተደበርኩበት አለችኝ፡፡ ስሙን ስትነግረኝ አውቀዋለሁ፡፡ በጣም የምወዳት እህቴ ስለሆነች ጉዳቷን ስለማልፈልግ የልጁን መጥፎ እና ጥሩ ባህሪ ዘርዝሬ ነገርኳት፡፡ የማውቀውን ሁሉ አሳወኳት እና ‹‹ሳልነግርሽ ብቀር እና ህይወትሽ ቢበላሽ ህሊናዮን ይወቅሰኛል፡፡ ካወቅሽ በኋላ ምርጫው ያንቺ ነው ብዬ ተውኳት፡፡

       ስልክ ቁጥር ተለዋውጠው ስለነበር መደወል ጀመረ፡፡ ሴቶችን ብዙ ጊዜ ሲያታልላቸው የማየው አፍ ነው፡፡ እሱም ይህን የተረዳ ይመስለኛል በርትቶ አፉን ያሰራዋል፡፡ ወሬው ስለፍቅር ሆኖ ሁለት ነጥብ አራት ነጥብ ወላ ፉልስቶፕ አያውቀውም፡፡ ወሬው ሰለቸኝ በማለት ስልኬ ባትሪ ጨረሰ፣ አሰሪዮ መጣችብኝ… እያለች ስልክ ታጠፋበት ጀመረች፡፡ ከዛም አይነቱ ተቀይሮ ልጅቷ እስኪሰለቻት የፍቅር ቃላት ያዘሉ ሚሴጆች ስልኳን እያንኳኩ መልዕክት ሳጥን ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ታስነብበኛለች፡፡ ከተላከላት ደብዳቤ ያላነበብኩት አንድም የለም፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች የተገለበጡ እንግሊዘኛ የፍቅር ጥቅሶች ሞልተውታል፡፡ እወድሻለሁ …ቅብርጥሴ…ልጅት መልስ አልሰጥም ብላ እኔ ፊት ብትደነፋም ደበቅ ብላ አንዳንዴ ትልክለታለች፡፡

     ወደ ሌላ ታሪክ ልውሰዳችሁ እና አመለወርቅ ትባላለች፡፡ የመን እንደገባሁ በግሩፕ ሲኖሩ ካስጠጉኝ ልጆች አንዷ ነች፡፡ የችግሬ ሰዓት ነች፡፡ ልታገባ ነው ተባለ እና ደስ አለኝ፡፡ ይህን ወሬ እንደሰማሁ ጥቂት ቀናት አልፈውት ያለሁበት ሱቅ ድረስ መጣች፡፡ ልታገባ እንደሆነ መስማቴን እና ደስታዋ ደስታዬ እንደሆነ ገለጽኩላት፡፡ ቅዝዝ፣ ትክዝ..ብላ እሱማ ቀረ እኮ…አለችኝ፡፡ ምክንያቱን እዚህ ጋር ብጽፈውም በማይጠቅም ምክንያት እንደቀረ ስትነግረኝ አዘንኩ፡፡ የሰውየውን ማንነት ስትነግረኝ በአጋጣሚ ህሊና አጠገቤ ነበረች፡፡ ደነገጠች፡፡ በስልክ፣ በSMS መልዕክት አላስቆም አላስቀምት ብሎኝ ቃሉን እስካፈረሰበት ሰዓት ይደውላል ይጽፋል አለችኝ፡፡ ሚሴጁን ልታሳየኝ ፍቃደኛ እንደሆነች ስጠይቃት አሳየችኝ ለአንዷ የጻፈውን ነው መሰለኝ ለሌላዋም የሚልከው ሁለቱም ስልክ ላይ ያለው አንድ አይነት ነበር… ለህሊናም ለአመለም የሚልከው፡፡

       በዚህ ተገርመን በሌላ ቀን ስናወራ አረ ለእኔም ይልክልኛል ብላ ሌላዋም ስልኳን አወጣች፡፡ አላማው ምን እንደሆን ባይገባኝም በየቤቱ የሚታደል የፍቅር ደብዳቤ መሆኑ ገረመኝ፡፡ ይህን ፍቅር እንበለው ልክፍት?    
        ቸር እንሰንብት

1 Comments:

At September 28, 2012 at 4:48 AM , Blogger ግሩም ዜና said...


በእርግጥ አልበም መጋበዝ በብዙዎች ዘንድ እንደ ባህል ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ታድያ ለዚህም መሰለኝ ብዙ ጊዜ ብዙ ቤት የፎቶ አልበም ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጠው፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ አንተ ማንም ሳጋብዝ ብድግ አድርግ በራስህ ግብዣ እራስህን የምትጋብዝበት አግጣሚ እና ያልጠበከው ነገር እስከ ማየት ትደርሳለህ፡፡ አንዳዴ ደግሞ ጓደኛህ አልያም የሄድክበት ሰው በሆነ ነገር ስለ ሆነ ሰው ሲወራ አልያም ሲነሳ እደንውም ፎቶው አለኝ ብሎ አልበም ከፍቶ ስለተወራው ሰው ማንነት ማረጋገጫ ይሰጥሃል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ ሻይ ቡና እስክትባል እንደ ማቆያም ሊቀርብልህ ይችላል ማየት አለ ማየት ምርጫው ላንተ ነው ይሄ የተለመደ ሲሆን ግሩም በሞቴ አልበም እንዳትግብዢኝ በሚለው ፅሁፍ ያነበብኩት ግን እንደ መታወቂያ በቦርሳ ይዞ ከመዞር ጀምሮ ሰው እስኪሰለቸው በየቦታውና በየዞሩበት የሚያሳዩ ከሆነ በጣም ይደብራል የሰዎችን ፍላጎት መንካትም ወይም መጫን ይመስለኛል፡፡

 

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home