እቴ ገላሽን ለውሻ እንደተሰጠ ቅንጣቢ አታራክሽው
እቴ ገላሽን ለውሻ እንደተሰጠ ቅንጣቢ አታራክሽው
ካደግሽበት ቤተሰብ ይህን ወርሰሻል?
በግሩም ተ/ሀይማኖት
አንዳንዴ ግርም የሚል ፎቶዎችን በአንዳንድ ነውረኛ
ድረ-ገጾች ላይ አያለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነታችንን፣ ባህላችንን፣ ማህበረሰባዊ ደንባችንን የሚጻረሩ እርቃኖች ለውስቢያ በተዘጋጀ ሁኔታ
ፎቶ ይነሳሉ፡፡ አንዳንዶቹማ በሀሳብ እየፈጸሙ መሆኑን ፎቶዎቹ አፍ አውጥተው ይናገራሉ፡፡ የሌሎቹ ደግሞ በአይናቸው የይለፍ ፍቃድ
ሰጥተው ‹‹ግባ በሞቴ!›› የሚሉ፣ የሚለማመጡ፣ በወሲብ ጥሜት የተንገላቱ ይመስላሉ፡፡ አይንና ከንፈራቸው ስሜትና ርሃባቸውን ያቃጥራል፡፡
በእውነት ስለ እውነት እንነጋገር እርቃን ፎቶ አይቶ ዘራፍ የሚልበት ፈላጊ አለ? የለም ማለቴ አይደለም፡፡ ልክስክስ እና ልፍስፍስ
አመል ያለው ሊሞቅብሽ ይችላል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ በየአጥሩ ስር ከሚሸና..እንትን በምን ይለያል? ሰለዚህ ገላሽን ለውሻ መደሰቻ እንደተሰጠ ልፋጭ አታርጊው፡፡ ያንቺ ንቀሽ አደባባይ የጣልሽውን ገላ አይቶ
በ___ርሃብ ጠኔ ሊጥለው የደረሰ ወይም እስር ቤት ከርሞ የወጣ በፎቶሽ ሊገነፍል ይችላል፡፡ በዳሽ ርሃብ ያልኩትን አደራ ጠበቅ
አድርጋችሁ እንዳታነቡት፡፡ መባለግ አልፈልግም፡፡ በነገራችን ላይ በር ዘግተሸ የምትሰሪውን በር ዘግተሸ አውሪው ማለቴ አይደለም፡፡
ሙች ነው የምልሽ አንቺ ያልተረዳሽው ብዙ ነገር
አንግበሽ ነው መከበሪያሽን መዋረጃ ያደረግሽው፡፡ ልብ በይ ደግሞ ውበትንም ሆነ መስህብነትን የሚይዘው ደበቅ ያለ ነው፡፡ አንቺ
ግን እንደ ልፋጭ ስጋ ቀንጥበሽ ጣልሽው፡፡ ስፖርተኛ ወደ ሜዳው ሲገባ እንደሆነ ልብስ የሚያወልቀው ሁሉ አንቺም ቦታሽን ለይ፡፡
እንደፍየል ጭራ ገመናሽን መሸፈን አቅቶሽ እንደቤርጎ ፖፖ ፊት ለፊት አትጣይው፡፡ በተወሰኑ ልቅ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሴቶችን እርቃን ፎቶ የሚለጥፉ ወንዶች ዝም ብለው ይመስልሻል?
አይምሰልሽ ዝቅጠት እና ክብረት ያዘለ አላማ አለው፡፡ ህሊናቸውን ሲያዘቅጡ የኪሳቸውን ያካብታሉ፡፡ አንዳንዶችም እንዳንቺው የሚያምር
ተክለሰውነት አለሽ ሲባሉ በአጉል ሙገሳ ተነስተው ነው፡፡ ሌሎቹም በአውሮፓና አሜሪካም ሆነ በአረብ ሀገራት ሊሸጡ የተዘጋጁ መደሰቻ
እቃዎች ማስታወቂያ መሆኑን እወቂ፡፡ በእርቃን ፎቶ ከመነሳት አንስቶ ሲወስቡ በቪዲዮ እስከ መቀረጽ የደረሱ እቃ ሆነው የቀረቡትን
እያየሽ ስልጣኔ መስሎሽ ራስሽን በርካሽ አትጣይው፡፡
ለምን ቤተሰብሽንስ ታሸማቅቂያለሽ? ከእነሱ ይህን ወርሰሻል? እርቃንሽን አደባባይ ስለወጣሽ ስልጣኔ መስሎሻል? አይደለም፡፡ የማንነት ማጣት ዝቅጠት ነው፡፡
ዛሬ እንደቀልድ የጣልሽው ማንነትሽን ነገ ዞረሽ ተሸከርክረሽ ብትፈልጊው አታገኚውም፡፡ ስልጣኔ ማለት ባህልሽን፣ የማንነት መገለጫሽን
አክብሮና ተከብሮ መኖር ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ የምታደርጊውን እወቂ ከጠቀመሽ ስሚኝ፡፡ ካፈለግሽ ግን አንቺ እና ማንነትሽ እንደተጣጣችሁ
ትኖራላችሁ፡፡
ስላም ሁኚ…
