የእናት ፍቅር.. በስደት ባህር ተሻግሮ እስከመከተል
የእናት ፍቅር.. በስደት ባህር ተሻግሮ እስከመከተል
ልጆቻቸውን ሊፈልጉ የተሰደዱት እናት በካንሰር በሽታ ይሰቃያሉ
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ምን ጊዜም የሚያሳዝን የሰዎችን ታሪክ ለመስማት የታደለው ጆሮዬ ግፍግፍ እስኪለው ሰምቷል፡፡ እየሰማሁ ነው ገና አሁንም እሰማለሁ፡፡ ነገሮች እስካልተስተካከሉ ድረስ፣ መንግስት ዜጋውን ህዝቤ እስካላለ ድረስ ወገኖቼ መጎዳታቸው አይቀርም፡፡ መጎዳታቸው እስካልቆመ ድረስ ይሰማል…ያሰማል…ይሰማል ለሌላ ያሰማል፡፡ ደከመኝ ሰለቸኝ አይሰራም፡፡ የሚያልቀው ወገን ነው፡፡ መፍትሄ መስጠት አቅም ቢያጥረኝ አቅም ያለው ወገን ወዳድ ሰምቶ መፍትሄ መስጠት ቢችል ‹‹ኡኡኡታዬን ሰምተሽ ተመለሽ በሞቴ…›› የሚለው የጥላሁን ገሰሰን ዜማ ‹‹ኡኡአታዬን ሰምታችሁ ፊታችሁን ወደ የመን መልሱ እባካችሁ…›› ብዬ አቀነቅናለሁ፡፡ ጆሮዬማ የሰው ጣር ከመስማት ከቦዘነ ዜግነቱን የረሳ ዝም ብሎ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ እያለ በባዶ ሜዳ የሚያቅራራ አስመሳይ ሆኗል ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት አምኖ ሀገሬን እወዳለሁ ብሎ አልሰማም ካለ…ጆሮዬ የስራ ማቆም አድማ አድርጓል ማለት ነው፡፡ ችግሩ ምንድን ነው? መፍትሄ እንስጠው ብለው ሌሎች ይህዋስ ሴሎቼ ሊመክሩ ይገባል እንጂ ዱላ መዘው አምባ ገነን ሆነው ስማ…ስማ ካሰማህ እናጠፋሀለን ብለው አይደሰኩሩም፡፡ በመተሳሰብ እና በመከባበር የተገነቡ ህዋሳት ናቸው አንድ ሰው አድርገው ያቆሙኝ፡፡ በመተባበር የተገነባች ኢትዮጵያም አንድ ሆና እንድትቆም ወገን የወገኑን ችግር ይስማ……ያሰማ……መፍትሄ ይሻት፡፡
ስልኬ አይናፋር ልጃገረድ ይመስል (ውይ በድሮው አስቤ ነው አንዳንዶች ዘንድሮ አይናፋር ልጃ-ገረድ የለም ይላሉ፡፡) ኪሴ ውስጥ ተደብቃ ትጨፍራለች፡፡ እንደጎጃም እንቅጥቅጥ ጭፈራ ቡርቅ ቡርቅ ብላ ሰውነቴን ኮረኮረችኝ እና ምን ሆንሽ ለማለት አውጥቼ ደነቆልኳት፡፡ ‹‹…ሀሎ ግሩም ሱልጣን ነኝ፡፡ ሱልጣን እናቱ የታመሙበት አስታወስከኝ?..›› አለ፡፡ እናቱ ታመውበት ተጨንቆ ይሆናል የደወለልኝ ብዬ እንጂ እንደሌላው ጊዜ ቢሆን ‹‹..እንዴት ይረሳል..እንዴት ይረሳል..›› የሚለውም ዜማ እጋብዘው ነበር፡፡ የቅርብ ወደጄ ሆኖ ለእናቱ ህክምና ስንት ስንማከር ከርመን አስታወስከኝ? ይለኛል እንዴ? ለማንኛውም አልኩና
‹‹አወኩህ ምን ገጠመህ?››
‹‹እኔ፣ እናቴ፣ ሁለቱ ልጆቼ ሆነን ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን እባክህ UNHCR ዋናው ቢሮ ሻራ ባግዳድ ናልኝ፡፡..›› ሻራ ባግዳድ.. ባግዳድ(Bagdad ) መንገድ ማለት ነው፡፡ እስኪ ልወዝወዘው ልወዝወዘው በእግሬ የሚለውን ዘፈን በእግሬ የሚለውን በታክሲ እያልኩ እብስ….ስደርስ በፎቶው ላይ እንደምታዩዋቸው አራት ሆነው ለሰላማዊ ሰልፍ ቆመዋል፡፡ በጋሪ ላይ የምታዩዋቸው የልጁ ማለቴ የሱልጣን እናት ወ/ሮ ሸጌ መሀመድ…አጠገባቸው ልጃቸው ሱልጣን ሁለቱ ደግሞ የሱልጣን ልጆች ናቸው፡፡
ለምንድን ነው ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉትን የሚለውን ስናይ ውስጥ የሚነካ አሳዛኝ ታሪክ አለው፡፡ እንይ፡-…ሱልጣን ታሪኩን ሲያጫውተኝ አንተ፣ እህትህ፣ እናትህ ወደ የመን እንዴት መጣችሁ ላልኩት
‹‹በፊት ከእኔም ቀድማ የመጣችው እህቴ ናት…ከመጣች በኋላ ድምጽዋ ጠፋ…ፍለጋ መጣሁ፡፡ ስመጣ ግን ፍለጋ ብቻ ሳይሆን እኔም ችግር ስለነበረብኝ ሽሽትም ነበር ማለት እችላለሁ፡፡ እህቴን ግን አላገኘኋትም፡፡ መሞቷን የሚያውቋት ጓደኞቿ ነገሩኝ፡፡ ከዛ የእህቴን ነገር ምን ብዬ ለእናቴ ልንገራት ዝም ማለት መረጥኩ እና ዝም አልኩ፡፡ ሁሌም ስልክ ስደውል ጥያቄዋ ልጄ እንዴት ሆነች ነው፡፡ አገኘሀት ነው ጥያቄዋ ተሳቀኩኝ፡፡ በቃ ጠፋሁባት፡፡ እኔም መጥቼ ስጠፋባት እናቴም ፍለጋ ስቃዩዋን አይታ በባህር መጣች፡፡ አስብ እስኪ ዛሬ 60 አመቷ ነው፡፡ ከመጠች አምስት አመት ሆኗታል፡፡ ዛሬ ዊልቸር ላይ ያየሀት ምክንያት በባህር መጥታ አግኝታኝ የእህቴን ሞት ስትሰማ በድንጋጤ ወደቀች፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ታመመች፡፡
ጡቷን ስትወድቅ የመታት ነገር ነበር መሰለኝ፡፡ እኔ በ UNHCR ስር ስለነበር ያለሁት እናቴንም መምጣቷን ነግሬ ፎረም ሞልቼ ነው ያለነው፡፡ በወቅቱ ግን ህክምና ባለማግኘቷ ወደ ካንሰርነት ተለወጠባት፡፡ ስኳር በሽታም አለባት ተባለ ከዛ በኋላ ነገሮች እየከረሩ እየተበላሹ ነው የመጡት፡፡ (UNHCR) ለህክምና የተለያየ ሆስፒታል ቢልካቸውም ሁሉም ከአቅም በላይ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ የውጭ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ዶክተሮቹ በቦርድ ወስነው ጽፈውላታል፡፡ እነሱ ግን እዚሁ እነምድትሞት የፈለጉ ይመስላል እስካሁንም ምንም ሊረዷት አልፈለጉም……አሁንስ ምን ደርሶ ይሆን? በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን ሀሳብ ይዤ እመለስበታለሁ፡፡

0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home