Thursday, April 25, 2013

አፍሪካ ስደተኞች



አፍሪካ
የመላ አፍሪካ የወንጀል ጉባዔ ባሕርዳር ላይ እየተካሄደ ነው

አፍሪካ ውስጥ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ እና ለሕገወጥም ጉዳዮች ማሸጋገር፣ መድኃኒቶችን፣ ማዕድናትን፣ እንደዝሆን ጥርስ የመሣሰሉ የተከለከሉ አደኖች ውጤቶችንና ሌሎችም ሃብቶችና ሸቀጣሸቀጥ በሕገወጥ መንገድ ማንቀሣቀስና ማስተላለፍ ሁል ጊዜ ችግር ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መንግሥታቸውን እየሸሹ በሚጠፉ ኤርትራዊያን ላይ እየተፈፀመ ነው የሚባለው አዲስ ዓይነት ንግድ ግን ቀድሞ ያልታየ አስፈሪና ዘግናኝ አድራጎት ታሪኮችን ፈጥሯል፡፡
የሲናይ ቁስልየሲናይ ቁስል

ኤርትራዊያኑ ስደተኞች ሱዳን ውስጥ ተጠልፈው ወደ ግብፅ ይሸጡና ቤተሰቦቻቸው ቤዛ የሚሆን ገንዘብ እስኪልኩ በስቃይ ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋሉ፡፡

ይህንንና መሰል ኢሰብአዊና ድንበር አቋራጭና የተደራጁ የወንጀል አድራጎቶችን አንስቶ የሚመክር የመላ አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሕርዳር ከተማ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

ሜሮን እስጢፋኖስ በባሕርዳሩ ጉባዔ ላይ ለመሣተፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የኤርትራ ተወላጅዋ ስዊድናዊት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሜሮን በቀን ከ15 እስከ ሃያ የሚደርሱ ኤርትራዊያን ስደተኞችን የስልክ ጥሪዎች ይቀበላሉ፡፡ ስብሰባው እየተካሄደ ሣለ ከቪኦኤ ጋር ለመነጋገር ወጣ ያሉ ጊዜ የእጅ ስልካቸውን ሲመለከቱት የተደረደሩት ያመለጧቸው ወይም ያልመለሷቸው ስልኮች ብዛት ያስደነግጥ ነበር አለች፤ የዚህ ዘገባ አጠናቃሪ ሃና ማክኔሽ፡፡

ሜሮን የሚያነጋግሯቸው ብዙዎቹ ኤርትራዊያን የሚደውሉት በሚደርስባቸው በጠላፊዎቻቸው ወይም በገዥዎቻቸው በሚደርስባቸው ሥቃይ መከራቸውን እያዩ ነው፡፡

“እያሰቃዩሽ ቤተሰቦችሽ ወይም ወላጆችሽ ጋ ይደውላሉ፡፡ እኔ ከአንዲት ልጅ እናት ጋር ተነጋግሬ ነበር፡፡ ልጅዋ በአምስት ወንዶች ስትደፈር እንድትሰማ ያደርጉ ነበር፡፡ የማስለቀቂያው ክፍያ ከሰላሣ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ ዶላር ይደርሣል፡፡ አማራጭ ስታጣ፣ ካለህ ትከፍላለህ፤ ካለበለዚያም ትሞታለህ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አድራጎት እየተፈፀመ ያለው እአአ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ግን እያየ እንዳለየ መሆንን መርጧል፡፡” ብለዋል ሜሮን እስጢፋኖስ፡፡
ሲናይሲናይ

እሥራኤል የአፍሪካዊያን ስደተኞችን የሥራ ፍቃድ በመንጠቋና ዓለምአቀፍ ለጋሾች ደግሞ ወደአውሮፓ የሚነጉደውን የስደተኛ ማዕበል ገታ እንዲያደርጉላቸው ለቀድሞው የሊብያ መሪ ሙአማር አል ከዛፊ ሰጥተው ስለነበረ ቀደሞ ሕገወጥ አስተላላፊ የበሩት አሁን የተያያዙትን አዲሱን ዓይነት የሥቃይ ንግድ ጀመሩና ገበያውንም አደሩት፡፡
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ

ድንበር እያቋረጠ የሚያመልጥ ዜጋ ቢገኝ ተኩሶ የሚገድለውን የኤርትራን መንግሥት እየሸሹ ከሃገር የሚጠፉ ኤርትራዊያን ቁጥር በወር ወደ ሦስት ሺህ እንደሚደርስ አንድንድ የረድዔት ድርጅቶች ይናገራሉ፡፡
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር እንደሚለው በመላ አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ከሩብ ሚሊየን በላይ ኤርትራዊያን ስደተኞችና ወደ 15 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ይገኛሉ፡፡

የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ ከሃገር ለመውጣታቸው እንዲከፍሉ ያደረጋል እየባለ ይወቀሣል፡፡ ሸሽተው የወጡ ሰዎችን ቤተሰቦች እንደሚቀጣ፣ በውጭ ሃገሮች የሚገኙ ኤርትራዊያን ከገቢያቸው 2 ከመቶ ታክስ እንዲከፍሉ በገሃድ የማይታዩ ግን አስገዳጅ የሆኑ ዘዴዎችን እንደሚጠቀም ይነገራል፡፡
ሲናይሲናይ

ተደጋግሞ እንደሚሰማውና ዓለምአቀፎቹ ድርጅቶችም እንደሚሉት ብዙ ኤርትራዊያን ሱዳን ውስጥ ከሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ሠፈሮች እየታፈኑና እየተጠለፉ ግብፅ ውስጥ ላሉ በደዊኖች ለሚባሉ የተለያዩ ጎሣዎች አባላት ይሸጣሉ፡፡

ከስዊድን የፖለቲካ ወገናዊነት የሌለው የኤርትራ ዜና የራዲዮ ሥርጭት ሥራ የሚያካሂዱት ሜሮን እስጢፋኖስ ሁሉም እጁን አጣጥፎ ባለበት ሁኔታ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ የጭካኔ አድራጎቶች እንደሚካሄዱ ይናገራሉ፡፡ “በየቀኑ ለአራት ሰዓታት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸንክረው ይሰቅሏቸዋል፡፡ ወንዶቹንም ሴቶቹንም በቡድን ይደፍሯቸዋል፡፡ ታጋቾቹ እርስ በራሣቸውም እንዲደፋፈሩ ያስገድዷቸዋል፡፡” ብለዋል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡

“በሺሆች የሚቆጠሩ በእንዲህ ዓይነት ጠለፋና ሥቃይ ውስጥ አልፈዋል” የሚሉት ሜሮን ወደ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ አሁንም በጠላፊዎቹ እጆች ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
የሲናይ ጠባሣየሲናይ ጠባሣ

በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ኅብረት ተጠሪ አሌክሣንደር ሮንዶስ “ይህ ዓለም ሊነቃበት የሚገባ ችግር ነው” ይላሉ፡፡ “ለምን እንዲህ ዓይነት ይደረጋል ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ እንዲህ ዓይነት አስፈሪና ቀፋፊ ነገር አሁን እየተፈፀመ መሆኑን መረዳት ይከብዳል፤ ይህ ዓይነተኛ የፍፁም ግድየለሽነት መገለጫ ነው፡፡” ብለዋል ሚስተር ሮንዶስ፡፡

የዚህ “ዝም የተባለበት አሣዛኝ ታሪክ” ሲሉ ሮንዶስ የጠሩት አድራጎት ወሬ “በዓለም ሁሉ መናኘት፣ ለዓለም ሁሉ መሰማት አለበት” ብለዋል፡፡
በሲናይ የበደዊኖች መንደርበሲናይ የበደዊኖች መንደር

“ሰዎች ይህንን ታሪክ ከነ ሙሉ ዘግናኝነቱ ወይም አስፈሪነቱ ነው ማወቅ ያለባቸው፡፡ ይህ እራሱን የቻለ የባርያ ንግድ ዓይነት ነው፡፡ ቁጥሩ ሊገለፅ የማይችል ገንዘብ የባሕር ላይ ውንብድናን ወይም ፓይረሲን ለማስወገድ እናፈስሣለን፡፡ ይህኛው ግን እጅግ የባሰ በሰው ሕይወት ላይ የሚመነዘር በርካታ መዘዝ ያለው የውንብድና ዓይነት ነው፡፡” ሲሉ አክለዋል የአውሮፓ ኅብረቱ ተጠሪ፡፡

ሰዎቹ በብዙ ሃገሮች ውስጥ እያለፉና እየተሸጋገሩ ሕገወጥ ማስተላለፍንና የሰው ንግድን ለማስወገድ አንዳች እርምጃ ያለመወሰዱ የሚያሣየው አንዳች የተቀነባበረ የሙስና ሴራ ሊኖር የመቻሉን ነገር ነው ይላሉ የአውሮፓ ኅብረቱ ሮንዶስ፡፡
የሲናይ እንባየሲናይ እንባ

በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ንግድ የሚካሄደው በሃያ አምስት ቤተሰቦች ወይም ጎጦች መሆኑንና በፍጥነት ማጥፋት የሚቻል መሆኑን ሜሮን አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት አንድ የተጠለፈ እንግሊዛዊን ለማስለቀቅ በሲናይ ላይ ወረራ አካሂደው እንግሊዛዊውን ያስለቀቁት የግብፅ የፀጥታ ኃይሎች በሰንሠለት የታሠሩ፣ የተደበደቡ፣ በረሃብ የደከሙ፣ የጭካኔና የሥቃይ አያያዝ እየተፈፀመባቸው እንደነበረ በግልፅ የሚታዩ ሌሎች ሰዎችን አግኝተው ሣያስለቅቋቸው መመለሳቸውንም ሜሮን ገልፀዋል፡፡
የሲናይ እንግልትየሲናይ እንግልት

ይህ የኤርትራዊያኑ መጠለፍ ጉዳይ ትልቅ ችግር መሆኑን የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር በዚሁ የኢትዮጵያው የወንጀል ጉዳይ ጉባዔ ላይ ማመናቸው ተዘግቧል፡፡

በግብፅም የወደቀው የሙባረክ አስተዳደር ባለሥልጣናት የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡

አራት ዓመታት ካለፉ በኋላ ግን ችግሩ ተወግዶ አልታየም፤ እንዲያውም በዓለም ገፅ ላይ እጅግ በበረታ ድኅነት ውስጥ የሚማቅቁ ሕዝቦች በሚኖሩበት ጥግ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ይህ ከመከራ የመገላገያ ቤዛ ክፍያ በብዙ እጅ አሻቀበ እንጂ፡፡
የሲናይ አሻራየሲናይ አሻራ

ይህ ስቃይና የሰው ልጅ መከራ ፍፃሜው ቅርብ እንዲሆን ብዙዎች ተስፋቸውን እየገለፁ ነው

Monday, April 22, 2013

እራስን በስራ ማሳየት !! እንደ ተመስገን ደሳለኝ!!

እራስን በስራ ማሳየት !! እንደ ተመስገን ደሳለኝ!!

Photo
ከሰሞኑ በመፅሔቶችና በጋዜጦች ያየሁት ትዝብት ምን አስታወሰኝ መሰላችሁ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በዚህ አመት ከአንድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በስድስት ኪሎ የሚገኙ እንዳንድ ምሁራንን እሳቸውን አስመልክቶ እነሱ የሚሏቸውን ሲናገሩ እሳቸው እኮ አደባባይ ወጥተው የሚናገሩት እህቱ እነሱ ጋር ስለምትሰራ ነው ይሉኛል፡፡ “እኔን የሚገርመኝ ነገር ወይ አደባባይ ወጥቶ መናገር ነው አለበለዛም ዝም ብሎ መቀመጥ ነው የሚሻላቸው” ሲሉ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ፡፡ እነዚህ ምሁራን ዶ/ሩ አደባባይ ወጥተው በመናገራቸው ከነሱ ዝምታ ጋር ሲላተም የሚያሰጣቸውን ስም ፈርተው እሱ እንዲህ ስለሆነ ነው ምናምን እያሉ ያስወሩበታል፡፡ ቢሆንም Prostitute Intellectual ከመባል አላመለጡም፡፡ እነዚህ ምሁራንም አንድ ሊቀበሉት ያልቻሉት እውነት አለ እሱም በፍርሀት ቆፈን ወስጥ መሆናቸውን ነው፡፡ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን መገዳደር የሚችሉት ፍርሀታቸውን አሸንፈው ወደአደባባይ በመውጣት እንጂ በአሉባልታ አይደልም፡፡ በስራ የበለጣቸውን በስራ ነው መብለጥ ያለባቸው፡፡ሰሞኑንም በፍትህ/አዲስ ታይምስ/ ልዕልና አዘጋጆች ላይ የሆነውም የሄው ነው፡፡ በአዘጋጆቹ ላይ ዘለፋ ሲያወርዱባቸው ቆይተዋል ዘለፋው አሁንም ቀጥሏል፡፡ እኔ አነ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ጓደኞቹ መተቸት የለባቸውም ከሚል አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በምን ጭብጥ ላይ ነው የሚተቹት? መተቸትም ካላቸው መተቸት ያለባቸው በሚሰሩት ስራ ላይ ነው፡፡ ተመስገን ከኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ያለውም ሁሉንም ጋዜጦች እና መፅሔቶች አይደለም፡፡ ተመስገን ለፕሬስ ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን ጋዜጠኞች ለነሱ ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር እንዳለው በበርካታ ፅሁፎቹ ላይ አስነብቦናል፡፡ ለዚህ ነው ጓደኞቼን መልሱልኝ ሲል ሲለምን የነበረው፡፡ለዚህ ነው እኔም የነዚህ ጋዜጠኛ ተብዬዎችን ተግባር ዘለፋ ያልኩት ሂስ እና ዘለፋ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ ከላይ እንደጠቀስከኳቸው የአ.አ ዪኒቨርሲቲ አንዳንድ ምሁራን እራሳቸውን ማየትን ያልፈለጉ ናቸው፡፡ በእውነት ምን እየሰሩ እንዳሉ ሊረዱ ፍቃደኛ ያልሆኑ ናቸውን ለዛ ነው በስራ የበለጣቸውን በዘለፋ ለማካካስ ደፋ ቀና የሚሉት፡፡ ጋዜጠኝነት ማለት እኮ እከሌ እንዲህ ሆነ እገሌ እንዲህ አለ ብሎ ማውራት አይደለም፡፡ የተንጫጩት ስራቸውን ስለሚያውቁ እና ክፍተታቸው ለህዝብ ስለተነገገረባቸው ነው፡፡ እንጂ የማይመለከታቸውን እማ አይመለከትም፡፡ ገንዘብ ተቀብለው የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱ በምን ሚዛን ነው መፅሔት ሆነ ጋዜጣ የሚባሉት፡፡ በምንስ ሚዛን ነው በጋዜጠኝነት ከሌላው አገር ወዳድ እና ለፕሬሱ ነፃነት መስዋትነት እየከፈሉ ከሚሰሩ ጋዜጠኞች ጋር በእኩል አይን የሚታዩት? እነዚህ ዘላፊዎች አሁንም እድሉ አላቸው፡፡ እራሳቸውንና ያሉበትን ሁኔታ በእውነት ተመልከተውና ከፍርሐታቸውም በፍጥነት ወጥተው በራሳቸው ስራ፣ ስም እና ምስል መምጣት ሲችሉ ነው፡፡ ካለበለዛ ምንም ዋጋ የለውም ያንድ ሰሞን መንጫጫት ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው!!፡፡

Thursday, April 18, 2013

“ማሪያም ነኝ” ባዩዋ ተፈረደባት

በአሸናፊ ደምሴ
የፌዴራሉ አቃቤ ህግ የማይገባትን ጥቅም ለማግኘት
በማሰብ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች በመንቀሳቀስ
ሰዎችን በማታለል “እኔ ማርያም ነኝ፤ እንደኢየሱስም
በጅራፍ ተገርፌያለሁ፤ ከሞትም ተነስቻለሁ፤
የወለድኳቸውንም ልጆች ያገኘሁት በመንፈስ ነው”
ስትልና የዓለም ፍፃሜ ደርሷል በሚል የሰዎችን የግል
ሀብት ለራሷ ስታደርግ ደርሼባታለሁ ሲል ክስ
የመሰርተባት የ34 ዓመቷ ትዕግስት ብርሃኑ ወ/
ጊዮርጊስ፤ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ወንጀል
ችሎት ፊት ቀርባ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ በ2 ዓመት
ከ4 ወራት ፅኑ እስራትና በአንድ ሺ ብር የገንዘብ
መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ባሳለፍነው ሳምንት ወሰነ።


እንደአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ከሆነ ግለሰቧ በአራት የተለያዩ ክሶች የተወነጀለች ሲሆን፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
“ለሰው ህይወት ማለፍ ሳቢያ ነች” ሲል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ያልተሟላ ነው ሲል ውድቅ ሲያደርገው በተቀሩት
ሶስት ክሶች ግን ጥፋተኛ ነች ብሎ እንድትከላከል ብይን ሰጥቶ ነበር።
ተከሳሿ ጥፋተኛ የተባለችበት አንደኛ ክስ በየካቲትና በመጋቢት ወራት ውስጥ 1999 ዓ.ም የማይገባትን ጥቅም

ለማግኘት አስባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 21 ልዩ ቦታው ኪዳነምህረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ300 በላይ
ሰዎችን በመሰብሰብ “እኔ ማርያም ነኝ፤ እንደኢየሱስም በጅራፍ ተገርፌ፤ ከሞትም ተነስቼያለሁ” የሚል የሀሰት ወሬ
በመንዛትና የዓለም ፍፃሜ ደርሷል ንብረት አያስፈልግም በሚል ያላችሁን ንብረት አምጡ ስትል ከተለያዩ የግል
ተበዳዮች ጥሬ ገንዘብና ወርቅ የተቀበለች ሲሆን፤ በአጠቃላይም 40ሺ ብር ለግል ጥቅሟ አውላለች ሲል በክስ መዝገቡ
ያስረዳል።
እንደአቃቤ ህግ ቀጣይ ክስ ደግሞ ተከሳሿ በሰኔ 1 ቀን 1999 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 16 ልዩ ቦታው
ላምበረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 50 የሚደርሱ ሰዎችን በመያዝ ወደደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጓዝ ወንጭ
ገዳም ተብሎ ወደሚጠራው መንፈሳዊ ቦታ በመውሰድ በፆምና ፀሎት ሰበብ አብረዋት የነበሩት ሰዎች ለአምስት ቀናት
ምግብ እንዳይበሉ በማድረግ እንዲዳከሙና ለከፋ ጉዳት እንዲዳረጉ አድርጋለች ሲል በክሱ ያትታል።
በሌላም በኩል ግለሰቧ በጥር 24 ቀን 2003 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ ቦታው ተክለሃይማኖት ቤተ-
ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ወደ 20 የሚጠጉ ህፃናት ልጆችና ሴት ተከታዮቿን በመያዝ፣ “እኔ ማርያም ነኝ፤ ልጆቼን
የወለድኳቸውም በመንፈስ ነው እንጂ ከወንድ ጋር ተኝቼ አይደለም” በማለትና ተከታዮቿም እርሷ ማርያም ነች።
ሞታም ተነስታለች እንዲሁም 40 ቀን ያለምግብ ትፆማለች በማለት ሀሰተኛ ወሬዎችን እንዲነዙ በማድረግ
ስታስተምር እንደነበር ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ ደርሶኛል ያለው ዐቃቤ ሕግ፤ በዚህም ምክንያት በቤተ-ክርስቲያኗ
ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ምዕመናን “ ሀሰት ነገር አትናገሪ” ሲሉ በመቃወማቸው ወደሁከት ውስጥ እንዲገቡ
ያደረገች በመሆኑ በፈፀመችው የሀሰት ወሬዎችን በማውራትና ህዝብን በማነሳሳት ወንጀል ተከሳለች ይላል።
ጉዳዩን ሲመረምረው የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ወንጀል ችሎትም የዐቃቤ ሕግን ክስ ተከሳሿ
ማስተባበል ባለመቻሏ ጥፋተኛ ሆና አግኝቻታለሁ ሲል፤ መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በ2 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ
እስራትና በ1000 ብር እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል።¾
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

Monday, April 1, 2013

እኔም እንዳቅሜ ሚጢጢዬ ትዝታ ፑሽኪን ውስጥ አለኝ

ወዳጄ አደም ሁሴንን የፑሽኪን ትዝታህ ሳየው ምላሽ ልሰጥ ግድ አለኝ፡፡ እኔም እንዳቅሜ ሚጢጢዬ ትዝታ ፑሽኪን ውስጥ አለኝ፡፡ ጋሽ አያልነህን በብዙ ነገር አድናቂው ብሎም አክባሪው ነኝ፡፡ ብዙ አማተር ገጣሚያን ያጡትን መድረክ አዘጋጅቶ እንኩ ያለ…ለጥበብ ስለጥበብ ብዙ የደከመ ነው፡፡ በተለይ ተተኪ ተዋንያን እና ገጣሚያን የማውጣቱን ነገር የእሱን ያህል የሰራ፣ የደከመ አላየሁም፡፡ ይህንን ስል የጋሽ ተስፋዬ አበበን ውለታ ረስቼ አይደለም፡፡ ጋሽ ተስፋዬ(ፋዘር) ራሱን የቻለ ቦታ ያስፈልገዋል፡፡
   አንቱ የተባሉትም ለወጣቶች እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ እና እነሱም እንዲከበሩ ለማድረግ ወርሃዊ የግጥም ምሽት  ማዘጋጀቱ በልቤ ውስጥ ቦታ እንድሰጠው ያደረገኝ ነገር ነው፡፡ ስንቶችንስ ለቁም ነገር አድርሷል? ስንቶች ከትላልቆች ትምህርት እንዲቀበሉ አድርጓል? እናንተው መልሱት፡፡ እኔ ጽሁፌን ሳሳየው አንተ ጸሀፊ የመሆን ተስፋ የለህም ያለኝ ታዋቂ ደራሲን ሳስታውሰው ያናድደኛል፡፡ እሱን ለማግኘት የደከምኩበትን ጊዜም ሳስብ ያበሳጨኛል፡፡ በእርግጥ እሱ በሰጠኝ አስተያየት ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ ይባስ ጠነከርኩኝ፣ እልህ ተጋባሁኝ፡፡ እነዚህ አይነት አማተርን የሚያጫጩ ባሉበት ቦታ ጋሽ አያልነህን ማየት ምንኛ መታደል ነው፡፡
አደም ሁሴን ‹‹..አርቲስት ጥላሁን ገሰሰም አንድ የጋሽ አያልነህን ቲያትር ይሰራል እየተባለ በምን ምክንያት እንደቀረ አላውቅም ወይም ስራ እንዴ…? …… ብቻ ግን ያስቆጫል አንድ ቲያትር ተውኖ ቢሆን ኖሮ እንዴት ደስ ይል ነበር…….!›› ብለህ ነበር በዝክረ-ጽሁፍህ አዎ! ተብሎ ነበር፡፡ ግን አልሰራም፡፡
አንደኛ ጋሽ አያልነህ ካለበት ተደራራቢ ስራ አንጻር በወቅቱ ቶሎ ጽፎ መስራት አልቻለም፡፡ ሁለተኛ ጥላሁንም በተለያየ ወቅት ለስራ፣ ለህክምናም በተደጋጋሚ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር፡፡ በኋላም እግሩ ላይ ችግር ከመድረሱ ጋር ተከትሎ ነገሮች አልተገናኝቶም እንደሚሉት ሆኑ፡፡ ‹‹..ግን ያስቆጫል አንድ ቴያትር ተውኖ ቢሆን እንዴት ደስ ይል ነበር..››ላልከው ሁለት ቴያትሮች ሰርቷል፡፡
በ1946 እና በ1947 ሀገር ማህበር በነበረበት ጊዜ ‹‹መንገደ ሰማይ›› እና የሁለተኛውን ርዕስ በደንብ ባላስታውሰውም ‹‹የተኮነነች ነፍስ›› ይመስለኛል፡፡ ሁለቱም ላይ በብቃት የተውኖ እንደነበር የሞያ ጓደኞቹ 60ኛ አመቱን በሀገር ፍቅር ባከበረበት ወቅት ገልጸዋል፡፡