እራስን በስራ ማሳየት !! እንደ ተመስገን ደሳለኝ!!
እራስን በስራ ማሳየት !! እንደ ተመስገን ደሳለኝ!!

ከሰሞኑ በመፅሔቶችና በጋዜጦች ያየሁት ትዝብት ምን አስታወሰኝ መሰላችሁ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በዚህ አመት ከአንድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በስድስት ኪሎ የሚገኙ እንዳንድ ምሁራንን እሳቸውን አስመልክቶ እነሱ የሚሏቸውን ሲናገሩ እሳቸው እኮ አደባባይ ወጥተው የሚናገሩት እህቱ እነሱ ጋር ስለምትሰራ ነው ይሉኛል፡፡ “እኔን የሚገርመኝ ነገር ወይ አደባባይ ወጥቶ መናገር ነው አለበለዛም ዝም ብሎ መቀመጥ ነው የሚሻላቸው” ሲሉ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ፡፡ እነዚህ ምሁራን ዶ/ሩ አደባባይ ወጥተው በመናገራቸው ከነሱ ዝምታ ጋር ሲላተም የሚያሰጣቸውን ስም ፈርተው እሱ እንዲህ ስለሆነ ነው ምናምን እያሉ ያስወሩበታል፡፡ ቢሆንም Prostitute Intellectual ከመባል አላመለጡም፡፡ እነዚህ ምሁራንም አንድ ሊቀበሉት ያልቻሉት እውነት አለ እሱም በፍርሀት ቆፈን ወስጥ መሆናቸውን ነው፡፡ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን መገዳደር የሚችሉት ፍርሀታቸውን አሸንፈው ወደአደባባይ በመውጣት እንጂ በአሉባልታ አይደልም፡፡ በስራ የበለጣቸውን በስራ ነው መብለጥ ያለባቸው፡፡ሰሞኑንም በፍትህ/አዲስ ታይምስ/ ልዕልና አዘጋጆች ላይ የሆነውም የሄው ነው፡፡ በአዘጋጆቹ ላይ ዘለፋ ሲያወርዱባቸው ቆይተዋል ዘለፋው አሁንም ቀጥሏል፡፡ እኔ አነ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ጓደኞቹ መተቸት የለባቸውም ከሚል አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በምን ጭብጥ ላይ ነው የሚተቹት? መተቸትም ካላቸው መተቸት ያለባቸው በሚሰሩት ስራ ላይ ነው፡፡ ተመስገን ከኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ያለውም ሁሉንም ጋዜጦች እና መፅሔቶች አይደለም፡፡ ተመስገን ለፕሬስ ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን ጋዜጠኞች ለነሱ ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር እንዳለው በበርካታ ፅሁፎቹ ላይ አስነብቦናል፡፡ ለዚህ ነው ጓደኞቼን መልሱልኝ ሲል ሲለምን የነበረው፡፡ለዚህ ነው እኔም የነዚህ ጋዜጠኛ ተብዬዎችን ተግባር ዘለፋ ያልኩት ሂስ እና ዘለፋ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ ከላይ እንደጠቀስከኳቸው የአ.አ ዪኒቨርሲቲ አንዳንድ ምሁራን እራሳቸውን ማየትን ያልፈለጉ ናቸው፡፡ በእውነት ምን እየሰሩ እንዳሉ ሊረዱ ፍቃደኛ ያልሆኑ ናቸውን ለዛ ነው በስራ የበለጣቸውን በዘለፋ ለማካካስ ደፋ ቀና የሚሉት፡፡ ጋዜጠኝነት ማለት እኮ እከሌ እንዲህ ሆነ እገሌ እንዲህ አለ ብሎ ማውራት አይደለም፡፡ የተንጫጩት ስራቸውን ስለሚያውቁ እና ክፍተታቸው ለህዝብ ስለተነገገረባቸው ነው፡፡ እንጂ የማይመለከታቸውን እማ አይመለከትም፡፡ ገንዘብ ተቀብለው የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱ በምን ሚዛን ነው መፅሔት ሆነ ጋዜጣ የሚባሉት፡፡ በምንስ ሚዛን ነው በጋዜጠኝነት ከሌላው አገር ወዳድ እና ለፕሬሱ ነፃነት መስዋትነት እየከፈሉ ከሚሰሩ ጋዜጠኞች ጋር በእኩል አይን የሚታዩት? እነዚህ ዘላፊዎች አሁንም እድሉ አላቸው፡፡ እራሳቸውንና ያሉበትን ሁኔታ በእውነት ተመልከተውና ከፍርሐታቸውም በፍጥነት ወጥተው በራሳቸው ስራ፣ ስም እና ምስል መምጣት ሲችሉ ነው፡፡ ካለበለዛ ምንም ዋጋ የለውም ያንድ ሰሞን መንጫጫት ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው!!፡፡
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home