Friday, June 28, 2013

ከ 110 በላይ ኢትዮጵያዊ ባህር ላይ ቀሩ

ከ 110 በላይ ኢትዮጵያዊ ባህር ላይ ቀሩ
ስለ ስደተኛው የቁራሌው ጩኸት እስከ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ….
         በግሩም ተ/ሀይማኖት
 ‹‹…ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚ ሀይሎች ከጅቡቲ ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው ነበር፡፡ ብዙ እናውቀለን…›› ይህን በስደት ዙሪያ የአዞ እንባ ያነባው ኢቲቪ ለውይይት ከጋበዛቸው ውስጥ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ያዳለጣቸው ነው፡፡ ያዳለጣቸው ያልኩት መንግስት ያን ሁሉ ማስመሰያ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አባሳደሩ በግልጽ ሳያውቁ ስላስቀመጡት ነው፡፡ የስደተኛው ህይወት አሳዝኗቸው አይደለም፡፡ ተቃዋሚዎች ይዘው ሊጠቀሙባቸው ስለሚፈልጉ ወይም ስለሞከሩ ነገ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው፡፡ ያ-ካልሆነማ ስንት አመት በሙሉ በስደት ወገን ረገፈ ሲባል…ሲጮህ ዝም በዝምታ ብለው በስደተኛው የጣር ድምጽ ባላላገጡ ነበር፡፡ ግን የፈሩት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የትጥቅ ትግል ሊያደርጉ መሰናዶ ላይ ስለሆኑ ከሆነ አንድ ሰሞን አራግበው ዝም ማለት ጦሱ እንደሚብስ ለምን ልብ አላሉትም? የወጣውስ በአግባቡ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ካልተደረገ ወዴት እንደሚያቀና እንዴት አላገናዘቡም? ይገርማል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ወዴት እያመራ ይመስላቸዋል? ለምንስ ያን አያስቡም? እንደ ዜግነቱ የሀገሩ ኤምባሲ ሊከራከርለት ሲገባ፣ ወደ ሀገሩ ሊመልሰው ሲገባ ኮሚኒቲ የሚባለው ውስጥ ተፋፍጎ ሶስት እና አራት አመት እንዲቀመጥ የአእምሮ መታወክ እንዲገጥመው ሲደረግ፣ በሽተኛውም ጤነኛውም በአንድ ቦታ እንዲቆይ ሲደረግ…ትኬት የሚቆርጥልህ ቤተሰብ ከሌለህ…ያመጣችሁ ሰው ትኬት ይቁረጥላችሁ..ተብሎ ከእሱ ዜግነት ይልቅ ለብር ክብር ሲሰጥ ሲያይ..ሀገሬ ባላት ኤምባሲ ሲበደል ለምንስ አይከፋው? ለምንስ አማራጭ አይወስድ? አንድ ሰሞን ሆይ ሆይ ብሎ ፖለቲካ ለማሳመሪያ ፕሮግራም ማድመቂያ ማራገብስ ውጤት ያመጣል? አያመጣም፡፡ መንግስት ህዝብን እያታለለ እስከመቼ የሚጓዝ ይመስለው ይሆን? ህዝቡ እኮ ያውቃል፡፡ ሳዑዲያ ፣ የመን.. እየተጨቆነ ያለው ወገኑ አይደለ እንዴ? ቤተሰቡ አይደለ እንዴ? ታዲያ የአንድ ሰሞን የሚሊኒየም አዳራሽ እና የኢቲቪ ለቅሶ የአዞ እንባ አልሆነም? ሆነ፡፡
   አስተዳዳሪዬ ባይላቸውም አስተዳዳሪህ ነን ብለው ላዩ የተጎበሩበት ሰዎች እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ድረስ በውሸት ሲደልሉት፣ አፋቸው ሌላ ስራቸው ሌላ ሲሆንበት ቢጠላቸው ምን ሊደንቅ? ምንም፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትጥቅ ትግል ስደተኞችን ሊጠቀሙባቸው ብቻ ሳይሆን ስደተኛው ሀገሩ መመለስ ካልቻለ እሱ ራሱ ተቃዋሚዎችን ፍለጋ በዳዴ መሄዱ አይቀርም፡፡ በተቃዋሚዎች ተጠቅሞ መታገሉም አይቀርም፡፡ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ካሉት ላይ ልበደርና ‹‹…ከጅቡቲ ወስደው ተቃዋሚዎች ለትግል ሊጠቀሙባቸው…›› ቀርቶ ስለ ስደተኞቹ መኖርስ ተቃዋሚዎች ያውቃሉ ወይ? እንደሚያውቁ አቃለሁ ግን እነሱ ‹‹..አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም..›› እንዲሉ ሆነዋል፡፡ ስደተኛው ኢትዮጵያዊ የሆነ እስከማይመስል ድረስ ተቃዋሚዎችም ረስተውታል፡፡ የተሻለ ሀገር ቢሆን የሚሰደደው እና ዶላር መቁጠር ቢጀምር ግን እኛ ያላንተ ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ምን ሊያደርግ? መከራ እንጂ ዶላር ስለማይቆጥር አላስታወሱትም፡፡ መንግስት ግን መከራውን መስማቱን አይፈልግም እንጂ ከዚህ ችግር ተርፈው ከተማ ከገቡ ከኤምባሲው ምንም አይነት ግልጋሎት ቢፈልግ ጌሙ ፍራንካ ነው፡፡ ዜጋ ነህ ቅብርጥሴ…ምንትሴ አይሰራም፡፡ ገንዘብ ከያዘ የአማራ ልማት..የትግሬ ልማት..የእንትን ልማት…በቆዳ እስኪቀሩ መጋጡን እንደ ጅብ ይችሉበታል፡፡ እሰይ የወያኔ ኤምባሲ…ብራቮ ይህን ምስኪን ስደተኛ ተገፍቶም ተደፍቶም ያመጣውን በሰበብ አስባቡ ንጠቁ፡፡
     ደሀን የሚያስብ፣ ግፍ የሚፈጸምበት ስደተኛን የሚያይ የሚያስተውል መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ አልገጠመንም፡፡ ያው ሁሌም ዞረሽ..ዞረሽ እንደሚሉት አይነት ነው የሚገጥመን፡፡ ትላንት ከሶማሊያ ጋር አብረው ሀገራቸውን የወጉ ተቃዋሚዎች አይነት አሁንም አሉን ከግብጽ ጋር ለመሰለፍ ያቆበቆቡ፡፡ ሀገራቸውን ከጠላት ጋር ወግተው ስልጣን ማግኘት እንጂ የህዝቡ ቁስል ያላቆሰላቸው ተቃዋሚዎች አሁንም አፍርተናል፡፡ ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ሀገሬ ክብሬ.. የ3000 ዘመን ታሪክ እያሉ ቀረርቶ የሚያሰሙ መንግስት እና ተቃወዋሚ አሁንም አሉን፡፡ ባይኖሩ በቀሩብን፡፡ ኢትዮጵያ ሀገሬ ጋራሽ ሸንተረሩ ሜዳማ…የሚል ቀረርቶ እያንቃረሩ መሬትና አፈሩን የሚወዱ ህዝቡን ያላማከሉ መንግስትና ተቃዋሚ አሉን፡፡ አሉ ከተባለ….
      በሰቀቀን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ተሳቆ መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶት፣ ሀገሩን መርገጫ መላ አጥቶ ያለውን ዜጋ ማን አስታወሰው? ማንም፡፡ የመን ውስጥ ሀረጥ የሚባለው የአለም አወቀፉ ስደተኞች ድርጅት ካምፕ ውስጥ ያለውን ስደተኛ ቁጥር ማን ይቀንሰው? የኢትዮጵያ መንግስት ከስደተኛ ቢሮው ጋር በመተባበር ዜጎቼን እየሰበአሰብኩ ነው ሲል ይቃዣል፡፡ ከዚህ ቅዠት ግን መቼ እንደሚነቃ እና እንደሚሰራ ነው ግራ የገባን፡፡ ስደተኛው አሁንም ስቃይ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስደተኛው አሁንም ባህር እየተሻገረ ነው ያለው፤ ስደተኛው አሁንም ባህር ላይ እየሰመጠ ነው የለው፡፡ ከሳምንት በፊት ከጅቡቲ ወደ የመን ድንበር እየገሰገሰ ያለ ጀልባ በመሳሪያ ተመቶ ሰጥሟል፡፡ የጫናቸው ዜጎቻችን በሙሉ ባህር በልቷቸዋል፡፡ ወደ 120 ሰው እንደሞተ ወዲያው ሰማሁ እና ለማጣራት አለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ውስጥ እና ሜዲካል ሳን ፍሮንቴን (ድንበር የለሽ የህክምና ቡድን) ሰራተኞች ጋር ስልክ መታሁ፡፡ እነሱም ወሬውን አማቱት፡፡
    በመሳሪያ ነው የተመታው ስለተባለ ማን ነው የመታው የሚለውን ጨምሮ እንዲመልሱልኝ በመጠየቄ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ እንድንል ነገሩን አድበስብሰው እንዲያውም መረጃ ካገኘህ ስጠን አሉ፡፡ በሰዓቱ አስከሬን በመልቀም ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሰው ነው ደውሎ መረጃውን የመረጀኝ፡፡ ከሌሎች አካላት ለማጣራት እንደሞከርኩት ደግሞ በመሳሪያ ተመቶ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ሀይለኛ ንፋስ(ማዕበል) ያለበት ወቅት በመሆኑ ያሰጠማቸው ማዕበል ነው በመሳሪያ አልተመታም ብለውኛል፡፡ ጀልባው ተመታም አልተመታም ለእኛ ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ ባንዴ 120 አካባቢ አርግፈናል፡፡ ይሄ መንግስት ፍካሬውን ሳይጨርስ የሆነ ሁነት ነው፡፡ ያሳፍራል፡፡ መንግስት የስልጣን ዘመኑን ማራዘሚያ የወቅቱን ፖለቲካ ማስከኛ ለፈፈው የሳምንት ሆይ ሆታ ሳይፈዝ ይሄ መሆኑ ያወራል እንጂ መቼ ይሰራል፡፡ ማውራት እና መስራት ለየቅል ናቸው ያሰኛል፡፡ 

Saturday, June 22, 2013

ጉዞ ወደ ባብ አል-የመን (4)



 
በግሩም ተ/ሀይማኖት
  መጥቻለሁ ቀሪ እንዳታደርጉኝ….ሽቶው እንዴት ነበር? እንደ መርካቶ ሽንት የተሞላበት ሽቶ የለም አታስቡ፡፡ ታዲያ..ወደድክም ጠላህም ይህን ጽሁፋ ለማንበብ 1500 አመት ወደ ኋላ መመለስ አለብህ፡፡ አለበለዛ ብልጡ አብርሃ እንዴት አሮጌዋን ሰነዓ(ብብል የመንን) እንደገነባት ማየት አትችልም፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ከዛሬ የፖለቲካ ሰዎች እንዴት በአስተዋይነቱ ይሻል እንደነበር ማየት ማስተዋል አትችልም፡፡ ወቅቱ ላይ ተቀምጠህ ነው በምናብ መቃየት፡፡ ቀኝ ኋላ ዙርርርር…! በምናብህ 1500 አመት ወደ ኋላ፡፡
     አሁን ባብ አል-የመን እቅፍ ውስጥ ነኝ፡፡ ትንፋሽዋን ልተነፍስ፣ ሙቀቷን ልሞቅ፣ ግልማቷን ልገለምት፣ ግርግሯን ላዳምቅ፣ ውበቷን ላደንቅ፣ ታሪኳን ልዘክር….ይሄ ከላይ የምታዩት ባብ አል-የመን የሚባለው እና የመግቢያ በሩ ነው፡፡ ገበያው መሀል ስንገባ እጣን አለ ቡና አለ…እንትን አለ…የእንትን እንትንም አለ ለማለት ፈልጌ አይደለም የመጣሁት፡፡ ግን እላለሁ፡፡ ያየሁትን ስለሆነ ማለት ያለብኝ ባልፈልግም እላለሁ፡፡ እሱን ወደ ኋላ እናያለን፡፡ አሁን ንጉስ አብርሃ ማነው? ከኢትዮጵያስ እንዴት ሄዶ ነገሰ? የሚለውን ከየቦታው ያሰባሰብኩትን ፋይል እንበረብራለን፡፡ ታሪክ እንሰልቃለን፡፡ የእስልምና ሀዲሳት ስለ አብርሃ ካሉትም እንጠቅሳለን እናጣቅሰለን እናስጠቅሳለን፡፡ ሀሀሀሀሀሀ እነ እንትና እንጠቅሳለን ስል አይን አይኔን የምታዩኝ ለምንድን ነው? አሳፈራችሁኝ አይናችሁን ዞር አድርጉና ልቀጥልበት….
    ከክርስቶስ ልደት በኋላ 575 . ጀምሮ ንጉስ አብርሃ 50 ዓመታት ልጆቹ ኢዛና እና ሲዛና 22 አመት የመንን አስተዳድረዋል፡፡ታዲያ አብርሽ ያኔ ትሪፕ ብሎ ሰዎቹ ላይ የያዘው ሙድ ይሄው ሀበሻን እንዲጠሉ አድጓቸዋል፡፡ በጭፍጨፋ ሀይለኛ ነበር አሉ-በአልጋ፡፡ ታዲያ አሉ ነው፡፡ ግን ያሉንም የአያታቸውን አያት..አያት የነካባቸው ናቸው፡፡ አንድ ሴት ልታገባ ስትል ቀድሞ እሱ ‹‹ቃ!›› ካላረገ ማነው ወንድ የሆነ ልጁን የሚድር..ብለው ያሙታል፡፡ አይ አብርሃ አራዳ ነው እሱ እፍታውን እየነፋ እንደ አውራ ጎዳና መንገድ ከፍቶ መንገድ ሰርቶ ለአግቢው ያስረክብ ነበር፡፡ ሀይለኛ አራጅ ነው ድንግል ድንግሉን…ያኔ ድንግል ነበር ማለት ነው አሁን ቢሆን እሱም አያገኛትም፡፡ አምሮት አምሮት ይቀራል፡፡
    አንዴ አሉ…አሁንም አሉ ነው፡፡ ያው ባለታሪኮቹ ካወሩልን ነው፡፡ አግቢዎቹ በዙና ቢለው ቢለው አዳርሶ መጨረስ አቃተው፡፡ በቃ እንደ ታታሪ ገበሬ ያርሰዋል፡፡ ይሄኔ ስንቱን ዘርቶበት ይሆን? ለሱ ሳይደርሰው ደግሞ ማሳለፉን አልፈልገም በቃ! የቀሪዎቻችሁ ጋብቻ ከሳምንት በኋላ ብሎ ሰርጉን ሰረዘው፡፡..ተጋኖ ይሆን እንዴ እዚህ ጋር..ቆይ ኧረ! 50 ሰው በቀን ቢያገባ ያን ሁሉ ሲያርድ ሊውል ነው? እንዴ የእሱ እንትን ከእንትን ነው እንዴ የተሰራው? የማይዝለው..?
   በዚህ the year of elephant በተባለው ንጉስ አብርሃ ባስተዳደረበት ወቅት አሁን ያለችው ሰነዓ ከተማ ለአቢሲኒያ ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች። ጉድ በል ሸዋ..ሰነዓ የአቢሲኒያ ዋና ከተማ…ኧረ!.ይሄ ነገር ታሪክ ተዛብቶ ነው ተጣብቶ?(በተለያዩ የታሪክ መዝገቦች ሰፍሮ ያለ ሀቅ ነው) በዛ ዘመን (በ575 ዓ.ም አካባቢ) የተገነቡ ቤቶች ዛሬ ባብ አል-የመን /የየመን በር/ በሚባለው ኦልድ(የቀድሞው)ሰነዓ አካባቢ አሉ። የየመን ዋና የቱሪስት መስህብ ናቸው። ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ አመት በላይ ያስቆጠሩ 14000 የሚጠጉ ቤቶች አሉ። the year of elephant  የተባለው ለምንድን ነው ብላችሁ አሁን እንዳትጠይቁኝ በኋላ ስለምነግራችሁ ታገሱ፡፡ ንጉስ አብርሃ ከኢትዮጵያ መጥቶ የመንን እንዴት ሊያስተዳድር ቻለ? እዛ ገብር አልገብርም ደጃዝማች ከፊታውራሪ፣ ራስ ከንጉስ ይፋጃሉ በአቋራጭ የመን ከች ብሎ ማን ሰቀለው? እንደኛ በስደት ይሆን የመጣው..?..ይህ ለብዙዎቻችን መልስ ያላገኝ ጥያቄ ነበር፡፡ መልስ ለማግኘትም በየአቅጣጫው መረጃዎችን መቃኘት ግድ ብሎኛል፡፡ በእስልምና እምነት ዙሪያ ያሉ መጽሐፍት ማለትም በሀዲስም ጥሩ ተደርጎ ሰፍሯል፡፡ ከዛም ወስጃለሁ…
    ከተለያየ አቅጣጫ ባሰባሰብኩት መሰረት አብረሃ ወደ የመን ከመምጣቱ በፊት በኢትዮጵያ ያለው ንጉስ የጦር አበጋዝ ነው፡፡ (ከፈለጋችሁ ጄኔራልም በሉት) በወ    ቅቱ ኢትዮጵያ ላይ የነበረው ንጉስ የትኛውም መጽሀፍ ላይ ስሙ አልተጠቀሰም፡፡ አብርሃን ወደ የመን መላኩ አናዷቸው ወላ ስሙ ደብሯቸው ይሁን አልገባ ብሏቸው ሰፍሮ አላገኘሁትም፡፡ ግን በሌላ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚል ሁለት የፖላንድ ታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን ትርጉም ላይ ‹‹..በአፄ ካሌብ ጊዜ እንደሆነ እና ለካሌብ ሲገብር እንደነበር ጠቅሰውታል፡፡   
   አብርሃን መቼም ታምተንበታል በእኛነት ስሜት እንያዘውና አብርሽ ብለን እንጥራው፡፡ ከእሱ ጊዜ በፊት ዙኑዋስ የሚባል የየመን ንጉስ ነበር፡፡ ታዲያ ፈጣሪውን የሚያውቅ አይደለም፡፡ በጣኦትና ጥንቆላ የሚያምን እንደሆነም በሰፊው ይነገራል፡፡ ወይኔ ያኔ ቢሆን አባባ ታምራት የነበሩት…(ምፅ..ቁጭት) ታዲያ ጋሼ ዘኑዋስ ለህዝቡ እኔ ነኝ ፈጣሪያችሁ የሚል ትምክህተኛነትም ነበረበት፡፡ እዚህች ጋር አሁን መልአክ አድርገው ለመንፈሱ ከሚሰግዱለት የኛው ጋር ተመሳሰለብኝ፡፡ አረቦቹ ‹‹ርዕስ ሀገኩም መለሰ ዘንዋ ሳ?..›› ይላሉ፡፡ ፕሬዘዳንታችሁ መለስ ዜናዊ ለማለት ነው ግን ዘንዋ የምትለው በእነሱ አባት የሌለው ልጅ ማለት ነው፡፡ የእኛን ስም ለመጥራት ያላቸውን ችግር፣ አባባላቸውን እና መሳሳታቸውን ለማሳየት እንጂ አስበው መለሰ ዲቃላ ለማለት አለመሆኑን ያሉት አሰምርበታለሁ፡፡ ባይሆን በጥንቆላው አሁን ያሉት ባለስልጣኖች አህያ እየነዱ ነበር አዲስ አበባ የገቡት ሲባል ስምቻለሁ፡፡ ከዘኑዋስ ጋ እሱ ካመሳሰላቸው እንጃ…ኧረ ተውኝ እሱን ምን አገባኝ፡፡ የዘኑዋስ ግብረአበር ባለስልጣኖቹም እንደ እሱው ትምክህተኞች ናቸው፡፡
    ንጉስ ታዲያ ጠዋት ተነስቶ የዛሬ የአየር ሁኔታ ሜትሪዎሎጂ ትንበያ ሳይሆን የውሎውን ኮከብ ትንበያ ያስነብባል፡፡ ለንጉሱ የሚጠነቁል ሰው ነበር፡፡ በወቅቱ ለንጉሱ የሚጠነቁለው ሰው እድሜው ሲገፋና ሲያረጅ ነገሮችን መዘባረቅ ጀመረ፡፡ ድንገት ቢሞት እንኳን ንጉስ ያለ ጠንቋይ እንዴት መሽቶ ሊነጋላቸው? ምስኪን ንጉስ ጥንቆላ እንደሱስ አዳብት አድርጓቸው ይሆን? አባባ ጠንቋይ ደግሞ ለንጉሱ ያዝናሉ እና አንድ ወጣት የሚጠነቁል ለማሰልጠን ለንጉስ ዘንዋስ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ የዋህ ጠንቋይ ለሰው የሚጨነቅ፡፡ እሱ ሲያጃጅለው መክረሙ አንሶ ሌላ የሚያጃጅለው ሊያሰለጥንለት አሰበ፡፡ ንጉሱም አንድ ወጣት መረጠ፡፡ ከእንጨት መርጦ ለታቦት ከሰው መርጦ..ሆነና ይሄ ታሪካዊ ወጣት ተመረጠ፡፡ ባይመረጥ ኖሮ ዛሬም ሆነ ለነገው ታሪኩ ባልተጻፈ ነበር፡፡ ወጣቱም ጥንቆላ ለመማር ሲመላለስ ከአንድ ክርስቲያን መለኩሴ ጋር ይገናኛሉ፡፡ እሱ ስለ ሚያምንበት ትክክለኛ ፈጣሪው እግዚአበሄር ያስተምረዋል፡፡
   ልጁ የጥንቆላውን ትምህርት አልማርም ነቄ ብያለሁ አለ፡፡ ይቅርታ ቆይ ያኔ ነቄ የሚል ነገር ነበረ እንዴ? (ታሪክንም አራዳ እናድርጋት ብለን ተግተን እንሰራልን ቂ…ቂ…ቂ..) ንጉሱ ተቆጣ፣ ጦፈ.. በገነ…ጡርጥር ኢብነል ጡርጡር (ወሬኛ የወሬኛ ልጅ) ጥሩት አለ፡፡ ተጠርቶ አልቀርብም ለንጉስም አልሰግድም እኔ የፈጠረኝን አምላክ አውቄያለሁ አልፎገርም፡፡ ተነቃቃን…ብሎ አመጸ፡፡ ለንጉሱ አልሰግድ በማለቱ ዘኑዋስ ልጁን ሊገለው ፈለገ፡፡ ደጋግሞ ሊያስገድለው ሞከረ፡፡
     አልቻለም፡፡
     ልጁ ተይዞ ሰይፉን ቢሰነዝርበትም አልሆነለትም፡፡ ሊወጋውም አልቻለም፡፡ አልገደለውም፡፡ ይህ ልጅ ንጉሱን አንድ ነገር ይለዋል፡፡
     ለንጉሱ ያለው ‹‹ሕዝብ ሰብስበህ ይህ ልጅ በሚያምነው አምላክ ስም ብለህ ካልሆነ ልትገድለኝ አትችልም›› ይለዋል፡፡ 20.000 ሰው በተሰበሰበበት ‹‹በእሱ አምላክ›› ብሎ ገደለው፡፡ ሰዉ ሁሉ፣የእሱ ፈጣሪ ነው ፈጣሪያችን ብሎ አመነ፡፡ ንጉሱ ህዝቡን ጨፈጨፈ፡፡ በዚህን ጊዜ ያመለጠ አንድ ሰው ለሮማው ንጉስ ሄዶ ተናገረ፡፡ በወቅቱ ሀያል ከሚባሉት ንጉሶች የፋርስ፣ የሮማ፣የሀበሻ ንጉሶች ነበሩ፡፡ (ወይኔ ዛሬ ሀያል ተብለው እነ አሜሪካ ቅልልቦሽ ሊጫወቱብን….ደግነቱ እኛም ታሪኩን ብቻ ይዘናል፡፡ ‹‹እንዲህ ነበርን›› እያልን 3000 ዘመን ተኛን፡፡ ስንነቃ አለም ሀይሌ ገ/ስላሴ ሆኖ ሮጧል፡፡ አምልጦናል፡፡)  የሮማው ንጉስ ሮማ ለየመን ሩቅ በመሆኑ በቅርብ ላለው የሀበሻ ንጉስ ሄደህ ንገር ብሎ መልዕክት ጽፎ ሰደደው፡፡ እንደተባለውም አደረገ፡፡
     የሀበሻው ንጉስ ተናደደ እኛ እያለን ብሎ መልዕክተኛውን ገላመጠው፡፡ ቢሆንም ለሰራዊቱ አለቆች ንጉስ አሸንፋችሁ የመን በእኛ እጅ ቁጥጥር ስር እንድትሆን ብሎ 70.000 ጦር አዘመተ፡፡ የዛን ጊዜ የንጉስ ወታደር መሪና አለቃ የነበረው አሪያል ነበር፡፡ ምክትሉ አብረሃ ነው፡፡ ተዋግተው አሸነፉ፡፡ ንጉስ ዙኑዋስ የየመን ንጉስ ሸሽቶ ጠፋ፡፡
          ቆይ አንዴ ፈልጌ ካገኘሁ ላምጣው….