ጉዞ ወደ ባብ አል-የመን (4)
በግሩም
ተ/ሀይማኖት
መጥቻለሁ ቀሪ እንዳታደርጉኝ….ሽቶው እንዴት ነበር? እንደ መርካቶ ሽንት የተሞላበት ሽቶ የለም አታስቡ፡፡
ታዲያ..ወደድክም ጠላህም ይህን ጽሁፋ ለማንበብ
1500 አመት ወደ ኋላ መመለስ አለብህ፡፡ አለበለዛ ብልጡ አብርሃ እንዴት አሮጌዋን ሰነዓ(ብብል የመንን) እንደገነባት ማየት አትችልም፡፡
ያም ብቻ ሳይሆን ከዛሬ የፖለቲካ ሰዎች እንዴት በአስተዋይነቱ
ይሻል እንደነበር ማየት ማስተዋል አትችልም፡፡ ወቅቱ ላይ ተቀምጠህ ነው በምናብ መቃየት፡፡ ቀኝ ኋላ ዙርርርር…! በምናብህ 1500
አመት ወደ ኋላ፡፡
አሁን ባብ አል-የመን እቅፍ ውስጥ ነኝ፡፡ ትንፋሽዋን ልተነፍስ፣ ሙቀቷን
ልሞቅ፣ ግልማቷን ልገለምት፣ ግርግሯን ላዳምቅ፣ ውበቷን ላደንቅ፣ ታሪኳን ልዘክር….ይሄ ከላይ የምታዩት ባብ አል-የመን የሚባለው
እና የመግቢያ በሩ ነው፡፡ ገበያው መሀል ስንገባ እጣን አለ ቡና አለ…እንትን አለ…የእንትን እንትንም አለ ለማለት ፈልጌ አይደለም
የመጣሁት፡፡ ግን እላለሁ፡፡ ያየሁትን ስለሆነ ማለት ያለብኝ ባልፈልግም እላለሁ፡፡ እሱን ወደ ኋላ እናያለን፡፡ አሁን ንጉስ አብርሃ
ማነው? ከኢትዮጵያስ እንዴት ሄዶ ነገሰ? የሚለውን ከየቦታው ያሰባሰብኩትን ፋይል እንበረብራለን፡፡ ታሪክ እንሰልቃለን፡፡ የእስልምና
ሀዲሳት ስለ አብርሃ ካሉትም እንጠቅሳለን እናጣቅሰለን እናስጠቅሳለን፡፡ ሀሀሀሀሀሀ እነ እንትና እንጠቅሳለን ስል አይን አይኔን
የምታዩኝ ለምንድን ነው? አሳፈራችሁኝ አይናችሁን ዞር አድርጉና ልቀጥልበት….
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ575 ዓ.ም ጀምሮ ንጉስ አብርሃ ለ50 ዓመታት ልጆቹ
ኢዛና እና ሲዛና 22 አመት
የመንን
አስተዳድረዋል፡፡ታዲያ አብርሽ ያኔ ትሪፕ ብሎ ሰዎቹ ላይ የያዘው ሙድ ይሄው
ሀበሻን እንዲጠሉ አድጓቸዋል፡፡ በጭፍጨፋ ሀይለኛ ነበር አሉ-በአልጋ፡፡ ታዲያ አሉ ነው፡፡ ግን ያሉንም የአያታቸውን አያት..አያት
የነካባቸው ናቸው፡፡ አንድ ሴት ልታገባ ስትል ቀድሞ እሱ ‹‹ቃ!›› ካላረገ ማነው ወንድ የሆነ ልጁን የሚድር..ብለው ያሙታል፡፡
አይ አብርሃ አራዳ ነው እሱ እፍታውን እየነፋ እንደ አውራ ጎዳና መንገድ ከፍቶ መንገድ ሰርቶ ለአግቢው ያስረክብ ነበር፡፡ ሀይለኛ
አራጅ ነው ድንግል ድንግሉን…ያኔ ድንግል ነበር ማለት ነው አሁን ቢሆን እሱም አያገኛትም፡፡ አምሮት አምሮት ይቀራል፡፡
አንዴ አሉ…አሁንም
አሉ ነው፡፡ ያው ባለታሪኮቹ ካወሩልን ነው፡፡ አግቢዎቹ በዙና ቢለው ቢለው አዳርሶ መጨረስ አቃተው፡፡ በቃ እንደ ታታሪ ገበሬ ያርሰዋል፡፡
ይሄኔ ስንቱን ዘርቶበት ይሆን?
ለሱ ሳይደርሰው ደግሞ ማሳለፉን አልፈልገም በቃ! የቀሪዎቻችሁ ጋብቻ ከሳምንት
በኋላ ብሎ ሰርጉን ሰረዘው፡፡..ተጋኖ ይሆን እንዴ እዚህ ጋር..ቆይ ኧረ! 50 ሰው በቀን ቢያገባ ያን ሁሉ ሲያርድ ሊውል ነው?
እንዴ የእሱ እንትን ከእንትን ነው እንዴ የተሰራው? የማይዝለው..?
በዚህ the year of elephant በተባለው
ንጉስ
አብርሃ
ባስተዳደረበት
ወቅት
አሁን
ያለችው
ሰነዓ
ከተማ
ለአቢሲኒያ
ዋና
ከተማ
ሆና
አገልግላለች። ጉድ በል ሸዋ..ሰነዓ የአቢሲኒያ ዋና ከተማ…ኧረ!.ይሄ ነገር
ታሪክ ተዛብቶ ነው ተጣብቶ?(በተለያዩ የታሪክ መዝገቦች ሰፍሮ ያለ ሀቅ ነው) በዛ ዘመን
(በ575 ዓ.ም አካባቢ)
የተገነቡ
ቤቶች
ዛሬ
ባብ አል-የመን /የየመን በር/ በሚባለው ኦልድ(የቀድሞው)ሰነዓ አካባቢ አሉ። የየመን ዋና የቱሪስት መስህብ ናቸው። ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ አመት
በላይ
ያስቆጠሩ
14000 የሚጠጉ
ቤቶች
አሉ።
the year of elephant የተባለው ለምንድን ነው ብላችሁ
አሁን እንዳትጠይቁኝ በኋላ ስለምነግራችሁ ታገሱ፡፡ ንጉስ አብርሃ ከኢትዮጵያ መጥቶ የመንን እንዴት ሊያስተዳድር ቻለ?
እዛ ገብር አልገብርም ደጃዝማች ከፊታውራሪ፣ ራስ ከንጉስ ይፋጃሉ በአቋራጭ የመን ከች ብሎ ማን ሰቀለው? እንደኛ በስደት ይሆን
የመጣው..?..ይህ
ለብዙዎቻችን
መልስ
ያላገኝ
ጥያቄ
ነበር፡፡
መልስ
ለማግኘትም
በየአቅጣጫው
መረጃዎችን
መቃኘት
ግድ
ብሎኛል፡፡
በእስልምና
እምነት
ዙሪያ
ያሉ
መጽሐፍት
ማለትም
በሀዲስም
ጥሩ
ተደርጎ
ሰፍሯል፡፡
ከዛም ወስጃለሁ…
ከተለያየ አቅጣጫ ባሰባሰብኩት መሰረት አብረሃ ወደ የመን ከመምጣቱ በፊት በኢትዮጵያ ያለው ንጉስ የጦር አበጋዝ ነው፡፡ (ከፈለጋችሁ
ጄኔራልም በሉት) በወ ቅቱ ኢትዮጵያ ላይ የነበረው ንጉስ የትኛውም
መጽሀፍ ላይ ስሙ አልተጠቀሰም፡፡ አብርሃን ወደ የመን መላኩ አናዷቸው ወላ ስሙ ደብሯቸው ይሁን አልገባ ብሏቸው ሰፍሮ አላገኘሁትም፡፡
ግን በሌላ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚል ሁለት የፖላንድ ታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን ትርጉም ላይ ‹‹..በአፄ ካሌብ ጊዜ እንደሆነ
እና ለካሌብ ሲገብር እንደነበር ጠቅሰውታል፡፡
አብርሃን መቼም ታምተንበታል በእኛነት ስሜት እንያዘውና አብርሽ ብለን እንጥራው፡፡
ከእሱ ጊዜ በፊት ዙኑዋስ
የሚባል የየመን
ንጉስ
ነበር፡፡
ታዲያ ፈጣሪውን የሚያውቅ አይደለም፡፡ በጣኦትና ጥንቆላ የሚያምን እንደሆነም በሰፊው ይነገራል፡፡
ወይኔ ያኔ ቢሆን አባባ ታምራት የነበሩት…(ምፅ..ቁጭት)
ታዲያ ጋሼ ዘኑዋስ ለህዝቡ
እኔ
ነኝ
ፈጣሪያችሁ
የሚል
ትምክህተኛነትም ነበረበት፡፡ እዚህች ጋር አሁን መልአክ አድርገው ለመንፈሱ ከሚሰግዱለት
የኛው ጋር ተመሳሰለብኝ፡፡ አረቦቹ ‹‹ርዕስ ሀገኩም መለሰ ዘንዋ ሳ?..›› ይላሉ፡፡ ፕሬዘዳንታችሁ መለስ ዜናዊ ለማለት ነው ግን
ዘንዋ የምትለው በእነሱ አባት የሌለው ልጅ ማለት ነው፡፡ የእኛን ስም ለመጥራት ያላቸውን ችግር፣ አባባላቸውን እና መሳሳታቸውን
ለማሳየት እንጂ አስበው መለሰ ዲቃላ ለማለት አለመሆኑን ያሉት አሰምርበታለሁ፡፡ ባይሆን በጥንቆላው አሁን ያሉት ባለስልጣኖች አህያ
እየነዱ ነበር አዲስ አበባ የገቡት ሲባል ስምቻለሁ፡፡ ከዘኑዋስ ጋ እሱ ካመሳሰላቸው እንጃ…ኧረ ተውኝ እሱን ምን አገባኝ፡፡ የዘኑዋስ
ግብረአበር
ባለስልጣኖቹም
እንደ
እሱው
ትምክህተኞች
ናቸው፡፡
ንጉስ ታዲያ ጠዋት ተነስቶ የዛሬ የአየር ሁኔታ ሜትሪዎሎጂ ትንበያ ሳይሆን
የውሎውን ኮከብ ትንበያ ያስነብባል፡፡ ለንጉሱ የሚጠነቁል ሰው ነበር፡፡
በወቅቱ ለንጉሱ
የሚጠነቁለው
ሰው
እድሜው
ሲገፋና
ሲያረጅ
ነገሮችን መዘባረቅ ጀመረ፡፡ ድንገት ቢሞት እንኳን ንጉስ ያለ ጠንቋይ እንዴት መሽቶ ሊነጋላቸው? ምስኪን ንጉስ ጥንቆላ እንደሱስ
አዳብት አድርጓቸው ይሆን? አባባ ጠንቋይ ደግሞ ለንጉሱ ያዝናሉ እና አንድ ወጣት የሚጠነቁል ለማሰልጠን ለንጉስ ዘንዋስ ጥያቄ
ያቀርባሉ፡፡
የዋህ ጠንቋይ ለሰው የሚጨነቅ፡፡ እሱ ሲያጃጅለው መክረሙ አንሶ ሌላ የሚያጃጅለው ሊያሰለጥንለት አሰበ፡፡ ንጉሱም
አንድ
ወጣት
መረጠ፡፡
ከእንጨት መርጦ ለታቦት ከሰው መርጦ..ሆነና ይሄ ታሪካዊ ወጣት ተመረጠ፡፡ ባይመረጥ ኖሮ ዛሬም ሆነ ለነገው ታሪኩ ባልተጻፈ ነበር፡፡
ወጣቱም
ጥንቆላ
ለመማር
ሲመላለስ
ከአንድ
ክርስቲያን
መለኩሴ
ጋር
ይገናኛሉ፡፡
እሱ
ስለ
ሚያምንበት
ትክክለኛ
ፈጣሪው
እግዚአበሄር
ያስተምረዋል፡፡
ልጁ የጥንቆላውን ትምህርት አልማርም ነቄ ብያለሁ አለ፡፡ ይቅርታ ቆይ ያኔ
ነቄ የሚል ነገር ነበረ እንዴ? (ታሪክንም አራዳ እናድርጋት ብለን ተግተን እንሰራልን ቂ…ቂ…ቂ..) ንጉሱ ተቆጣ፣ ጦፈ.. በገነ…ጡርጥር
ኢብነል ጡርጡር (ወሬኛ የወሬኛ ልጅ) ጥሩት አለ፡፡ ተጠርቶ አልቀርብም ለንጉስም አልሰግድም እኔ የፈጠረኝን አምላክ አውቄያለሁ
አልፎገርም፡፡ ተነቃቃን…ብሎ አመጸ፡፡ ለንጉሱ አልሰግድ በማለቱ ዘኑዋስ ልጁን ሊገለው ፈለገ፡፡ ደጋግሞ ሊያስገድለው ሞከረ፡፡
አልቻለም፡፡
ልጁ ተይዞ ሰይፉን ቢሰነዝርበትም አልሆነለትም፡፡ ሊወጋውም አልቻለም፡፡ አልገደለውም፡፡
ይህ
ልጅ
ንጉሱን
አንድ
ነገር
ይለዋል፡፡
ለንጉሱ ያለው ‹‹ሕዝብ ሰብስበህ ይህ ልጅ በሚያምነው አምላክ ስም ብለህ ካልሆነ ልትገድለኝ አትችልም›› ይለዋል፡፡
20.000 ሰው
በተሰበሰበበት
‹‹በእሱ
አምላክ››
ብሎ
ገደለው፡፡
ሰዉ
ሁሉ፣የእሱ
ፈጣሪ
ነው
ፈጣሪያችን
ብሎ
አመነ፡፡ ንጉሱ ህዝቡን ጨፈጨፈ፡፡ በዚህን ጊዜ ያመለጠ አንድ ሰው ለሮማው ንጉስ ሄዶ ተናገረ፡፡ በወቅቱ ሀያል ከሚባሉት ንጉሶች የፋርስ፣ የሮማ፣የሀበሻ ንጉሶች ነበሩ፡፡
(ወይኔ ዛሬ ሀያል ተብለው እነ አሜሪካ ቅልልቦሽ ሊጫወቱብን….ደግነቱ እኛም ታሪኩን ብቻ ይዘናል፡፡ ‹‹እንዲህ ነበርን›› እያልን
3000 ዘመን ተኛን፡፡ ስንነቃ አለም ሀይሌ ገ/ስላሴ ሆኖ ሮጧል፡፡ አምልጦናል፡፡) የሮማው ንጉስ ሮማ ለየመን ሩቅ በመሆኑ በቅርብ ላለው የሀበሻ ንጉስ ሄደህ ንገር ብሎ መልዕክት ጽፎ ሰደደው፡፡ እንደተባለውም አደረገ፡፡
የሀበሻው ንጉስ ተናደደ እኛ እያለን ብሎ መልዕክተኛውን ገላመጠው፡፡ ቢሆንም ለሰራዊቱ አለቆች ንጉስ አሸንፋችሁ የመን በእኛ እጅ ቁጥጥር ስር እንድትሆን ብሎ 70.000 ጦር
አዘመተ፡፡ የዛን ጊዜ የንጉስ ወታደር መሪና አለቃ የነበረው አሪያል ነበር፡፡ ምክትሉ አብረሃ ነው፡፡ ተዋግተው አሸነፉ፡፡ ንጉስ ዙኑዋስ የየመን ንጉስ ሸሽቶ ጠፋ፡፡
ቆይ አንዴ ፈልጌ ካገኘሁ ላምጣው….



0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home