—

ተስፋዬ
ካሳ ጋር ይህችን ፎቶ ስቀበለው ‹‹ኪስ ቦርሳህ ውስጥ አልፋና ጨርቅ አድርገው ደሞ..›› ብሎኝ ነበር፡፡
በእርግጥም ኪስ ቦርሳዬ ውስጥ ደከም ብላ ተበሳቁላለች፡፡ መስክሩልኝ ጨርቅ ግን አልሆነችም፡፡ መሰከረም ወር ውስጥ
የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ ዘላለም ገብሬ አስታውሶ የጻፋትን ከተስፋዬ ጋር የተያያዘች መሪር ትንቢታዊ ቀልድ ዛሬም
ዳግም ላላያችሁት ላስፍር…ተሰፋዬን እወደዋለሁ፡፡ አብሶ ቅምቀማ ሙድ ላይ ይመቸኛል፡፡ ሰውነቴ ላይ ያሉትን ኮሚክ
ነርቮች ኦቨርታይም ሰርተው እንዲያመሹ ያደርጋቸዋል፡፡ በቃ! መሳቅ ነው፡፡ ‹‹ኤጭ አረ በዛ አገጠጥክ..›› ሲል
ሰብሰብ ማለት ነው፡፡ ለሆነ ጉዳይ ደብረዘይት ሄድኩና የባለቤቱን መሞት ሳልሰማ
ቀረሁ፡፡ ስንገናኝ ‹‹ደብረዘይት ሆኜ የሚስትህን ሞት በሬድዬ ነው የሰማሁት…›› አልኩት፡፡ ቀልዴን ቀላቅዬ፡፡
ችግር የለም የእኔን ደሞ በጋዜጣ ታነበዋልህ አለኝ፡፡ ይህ ነበር ለእኔም ሆነ ለጓደኞቼ መሪር ትንቢታዊ ቀልድ
የሆነብን፡፡ ለስራ ጉዳይ አርሲ አቦምሳ የሚባል ቦታ ሄድኩኝ፡፡ ከዛም አልፌ ተፈሪ ብርሃን…አርባጉጉ.. እያልኩ
የምቀጥልበት መንገድ ነበረና ከኢንፎርሜሽን ርቄያለሁ ስመለስ ናዝሬት ላይ የተስፋዬን ሞት ጋዜጣ ላይ አነበብኩ፡፡
በህይወቴ የሚገርም ገጠመኝ ከምለው አንዱ ነው፡፡
—
1 Comments:
ፍቅር የነበረና ፍቅር ሆኖ የሚኖር የመቼውም ምርጥ ኮሜድያናንችን ነበረ።እንወደዋለን እወደዋለሁ ሁሌም እንደዚህ ስላስታወስከን ደሞ እናመሰግንሃለን።
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home