ዜማና ፍቅር..ግጥምና ፍቅር
ዜማና ፍቅር..ግጥምና ፍቅር
ግሩም ተ/ሀይማኖት
አንዳንዴ
ሲገርመኝ ግርም ይለኛል፡፡ በቃ! እንዲሁ ከምድር ተነስቶ ግርም ይለኛል፡፡ ግን ስለ እውነት ከምድር ይነሳ ከሰማይ አለያም ከውስጤ…ተነስቶ
ይግረመኝ እንጃ!! እውነታው ግን ግርም የሚለኝ ብዙ ነገር ቢሆንም ይሄ ፌዝቡክ ለስንቶች መተንፈሻ ሆኖናል? እንዲያው እስኪ ዞር ዞር ልበል አልኩ እና ወክ ላደርግ ጀመርኩ፡፡ እዚሁ ፌዝቡክ ላይ
ነው እንጂ ፒያሳና አራ ኪሎ እንዳይመስሎት፡፡ ታዲያ ምን ይጠበስ እንዳይሉ…ፌስ ቡክ ላይ ምን ጠፍቶ ሁሉ በእጃችን ሁሉ በደጃችን
የሚጠበሰውም ጠባሹም ሞልቷል፡፡ ወክ ሳድርግ ራሱ ስንቱ ገጽ ላይ ጥብስ እና ጠባሽ..ኧረ ተጠባሹ ራሱ ብትሉ ሞልቷል፡፡ አሳው፣
ስጋው፣ ድንቹ፣ እንትኑ…እነ እንትና እነ እገሊት…በሽበሽ
ነው፡፡ አሁንም እዛው ፌዝቡክ ላይ ወክ ሳደርግ ያየሁትን ገገማ አጠባበስ ላውጋችሁ፡፡ ልጅት ክፍትፍት ብላ ተቀምጣ የተነሳችውን
ፎቶ ለጥፋለች፡፡ መከፋፈቷን ሳይ ኤልያስ ተባባል ክፍትፍት ነው ፌቷ..በሚል ያዜመው ቅኔያዊ ግጥም ትዝ አለኝ እና… ክፍት ብዬ
ተስደብኩ፡፡ ጊዜ እና ዘመን ሰለጠኝኩ ባይነት ሰንጎ ይዞን አንጂ ይሄ ፎቶ እንኳን አደባባይ ሊወጣ አልበም ውስጥ እንኳን ከፎቶ
ጀርባ የማይቀመጥ ነው፡፡ ለዚያውም ‹‹ይሄን ውዳቂሽን ይዘሽ ወዲያ ሂጂ..›› አይነት የተዘፈነበት ነው፡፡ ይህን ለማስረዳት አራዳዎቹ
ቢሆኑ በአጭሩ የሆላንድ ላም ነች ወተት ቤቱን እየው ይሉታል፡፡ ግን ነውር ነው አይባልም፡፡ ግዴታ ሸንቃጣ ብቻ ነው ፌዝቡክ ላይ
እርቃን ፎቶውን የሚለጥፈው? አምሯት አምሯት ትሙት እንዴ? በዛ ላይ ወንድ እና ቢላ ጮማ ይወዳል ይህን የስጋ ክምር ይዩት ብላ ይሆናል፡፡ ምስኪን የአይን ሻወር ወሳጆች ጮማ
ወዳዶች ምን አሉ? እንዲያው ሌላውስ ሰው ምን ይላል? ለማየት ኮመንት የሚለው ስር ቃኘሁ፡፡
‹‹ምርጥ ነው…ዋው! ምርጥ ነው…ስሜል ገርል…..››….ጠላታችሁ ክው ይበል
ሰዉ ገልብጦ ነው የሚያየው ወይስ መለኪያው በተቀሰቀሰው ስሜቱ ልክ ነው የሚተነፍሰው ብዬ አሰብኩ፡፡ ማሰቤ በማሰብ ውስጥ ተሰንጎ
ቀጠልኩ፡፡ ‹‹ውይ ቢገኝ እኔን አያርገኝ..›› ብሎ ስሜቱ ገደቡን የጣሰበት አስፍሯል፡፡
‹‹በህልሜ ነው በእውኔ ወይ በቴሌቪዥን
አይቼ ፈዘዝኩት አስደንጋጭ መልክሽን…›› የሚለውን ከአለማየሁ እሸቴ ተበድሮ
ሳያዜምላት አልቀረም፡፡ አንዱ ደግሞ ስልክሽን ላኪልኝ ብሎ ኮመንት ላይ ለጥፏል ጀገማ አልኩና አለፍኩ፡፡ ቀጠልኩ እና ጎዞዬን ከአንዱ
ጓደኛ ወደ አንዱ አደረኩ፡፡ አቤል ገብሩ የሚሉት ልጅ አለላችሁ፡፡ እንቅፋት ሆነብኝ (ወደ ሌሎች ከመሄዴ በፊት ያዘኝ) የበርካታ
ዘፋኞችን ግጥም ይጽፋል፡፡ ዋናው እንቅፋት የሆነኝ እና ዜማና ፍቅር..ግጥምና ፍቅር የሚለውን እንድጽፍ የጋበዘኝ፡፡
ትዝታና አቤል ተረዳድተው ወደኋላ መለሱኝ እና ልጽፍ ተነሳሁ፡፡ መትፎ
ልጅ ነው ፍቅር የያዛችሁ ሰዎች እሱን እንዳታነቡት…አያዋጣም፡፡ በፊት የተከዛችሁበት ዜማ ካል ግትሙን አስፍሮት ታያላችሁ፡፡ ግን
እኔም አቤልን ሰራሁለት ረገምኩት፡፡
ሁሌም ያጽፍህ ብዬ ረገምኩት፡፡እንዳጻፈኝ ያጽፈው፡፡ አስቡት እስኪ ‹‹ፍቅር›ስንት
ጊዜ ይይዛል›› ብሎ ይጠይቃል እንዴ? አቤል አሁን ማን ይሙት ስንቱን የዘፈን ግጥም
ገልብጠህ ስትለጥፍ ጥላሁንን ‹‹…ካንድም ሁለት ሶስቴ ፍቅር ጸንቶብኛል
ግን ዛሬ አዲስ ሆኖ..›› ሲል አልሰማሁም ለማለት ነው? ወይስ ጋሽ ጥሌ በርከት አድርጎ ስላፈሰው
ለየት አድርገህ አይተኸው ነው?
ቆይ ኧረ! ሰፋ አድርጌ ልመለስ….
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home