ዜማና ፍቅር.. ግጥምና ፍቅር
ዜማና
ፍቅር..
ግጥምና
ፍቅር
ግሩም ተ/ሀይማኖት
ግሩም ተ/ሀይማኖት
ዜማዎች ስለፍቅር
ይተነፍሳሉ፡፡ መተንፈስ ብቻ አይደለም እሪሪሪሪ…. ብለው ያቀልጡታል፡፡ ፍቅር የራሱም ዜማ አለው፡፡ ላስተዋለው ዜማው፣ ቅኝቱ..ውበቱ፣
ደም ግባቱ ያለው ስምረቱ (መስመሩ) ላይ ነው፡፡ ዜማ ውስጥ የሚከሸነው ግጥም በሚሰጠው መልዕክት አንጀታቸው የሚርስ የመኖሩን ያህል በትዝታ ገመድ ተሸብበው እህህን የሚያቀነቅኑ መኖራቸውም
የታወቀ ነው፡፡ ዜማ ለፍቅር፣ ዜማ ለትዝታ…ዜማ ለደብዳቤ..እርሶ የቱን ተጠቀሙ? ዘፈን በሚለው እንወሰድና ፍቅር
ሲይዞት ወይም ፍቅርን ለማድመቂያ ተጠቀሙበት ወይስ ያለፈውን ትዝታ ጎትቶ የሚያመጣ ትዝታ መቀስቀሻ አደረጉት? ወይስ ከዘፈን ውስጥ የመዘዙትን ግጥም ለደብዳቤ ማዳመቂያ ተጠቀሙበት? ለደብዳቤውም ሆነ ለትዝታው..
‹‹መጀመሪያ ማወቅ መተዋወቅ
ቀስ ብሎ በፍቅር መግባባት…››
የምትለውን እያንጎራጎርን ጉዞ ወደ ፍቅር እናድርግ…፡፡ ለመሆኑ ይሄ ፍቅር ግን ምን አይነት ሰቁልጢ ነገር ነው? አንዴ ዲዳ ያደርጋል
ደብዳቤ ያጽፋል፡፡ እውር ነው ይላሉ..ካላየ እንዴት ሄዶ ያዘ? አንዳንዴ ጠራቢም ያደርጉታል፡፡ ጠርቦ ጣለኝ ሲሉ ይሰማል፡፡ አንዳንዴ
ወቃጭም ያደርጉታል፡፡ አስቴር አወቀ ‹‹…ፍቅር ደቁሶኛል ስትል..›› ፍርጁን አብዝታዋለች፡፡
አራዳ፣ ሞኝም፣ ገገማም
ያርጉታል፡፡….ኧረ ምን ያላደረጉት አለ? ቆይ እስኪ እኔ
የማውቀው የቱን ነበር? አስታውሱኝ፡፡ ምግብ ይዘጋል ብለው ላሙት…ጠላቶትን እኔን ዘግቶኝ አያውቅም፡፡ እንዲያውም አፒታይዘር ነው
የሆነኝ፡፡ ድምጼ አውስትራሊያ ድረስ ይሰማል እና
አበባ መስክሪ፡፡ (ታዲያ አሁን አበባ ኤክስፖርት ማድረግ ስለጀመርን የተላከውን አይደለም ምስክር ያደረኩት፡፡
የራሴን…ነው፡፡) አቦ ሞኝ ይሁን አራዳ ብቻ ለፍቅር…ግጥሞቹን እንዴት ተጠቀምናቸው? በአንድ
ወቅት አንጋፋው ደራሲ ተርጓሚ ማሞ ውድነህ ከቢሯችን ብቅ ብለው ስንጨዋወት ከባለቤትዎ ጋር እንዴት ተገናኛችሁ የሚለውን ጥያቄ ሲመልሱ
(በነገራችን ላይ በቃለ-ምልልስ ወቅት አይደለም፡፡ በወዳጅነት ስናወራ ነው፡፡)
‹‹ስማኝ ያኔ ዘመኑ ደግ ነው፡፡ አንድ ትምህርት ቤት ነበር የምንማረው ደብደቤ
ጻፍኩና ሰጠኋት፡፡
‹‹..በፈረስ መጣ እያለ እሽክምክም..
አንቺን የኔ ካላደረኩ ሱሪ አላጠለኩም…›› የሚል ግጥም ነበረበት ያሉኝን አስታውሳለሁ፡፡
በነገራችን ላይ ጊዜው ከመርዘሙ ብዛት ዘንግቼ ቀንሼ ወ|ይ ጨምሬ ከሆነ ሳስታውሰው አስተካክላልሁ..በዚሁ ከፈረስ ጋር በተያያዘ
ሌላም አለ፡፡ እንሆ፡-
‹‹በፈረስ ነይ
እንጂ በሚገሰግሰው
መቼ በቅሎ ያውቃል
እንዳንቺ ያለ ሰው…›› ብለው ፍቅራቸውን በግጥም የሚገልጹም ሞልተዋል፡፡ አሁን ይህቺ ነገር ፋሽን አለፈባት ይሆን? በቃ! የፍቅር ደብዳቤ ሲጽፉ በግጥም አዳምቀው በስዕል አሸብርቀው….አይ ድሮ!...ድሮ..
ድሮ ቀረ እንበል እንዴ ይሄንንም፡፡ ኧረ አሁንም አለ፡፡ ከምር ግን ስንቶቻችን የፍቅር ደብዳቤ ጽፈን እናውቃለን?
‹‹ሮዝ አበባ ላይ አሞኝ
ተኝቻለሁ..
አይንሽን ካላየሁ እንዴት
እድናለሁ..››
የልብ ቅርጽ ተስሎ በጦር ሲወጋ…እርሶ እንዴት ነበር የጻፉት… ‹‹ላቭ ኢዝ ብላይንድ፣
ላቭ ኢዝ ኤ ዎንደርፉል፣…የመሳሰሉትን በስዕላ ስዕል ማጀብ…..ደስ የሚል ጊዜ፡፡ ለእርሶ እንዴት ነበር?
ላቭ ኢዝ ሚልክ
በት ኖት ድሪንክ ….›› ግን የፍቅር ደብዳቤ የሚጽፉትን ስናይ እኮ አስገራሚ አጻጻፍም
የነበራቸው አሉ፡፡ አስታውሳለሁ ሽፈራሁ የሚባል ልጅ
‹‹እኔስ ወድሻለሁ አሁንም ወድሻለሁ..ነገም ወድሻለሁ
ካጣሁ ግን ምን እሆናለሁ
እንዴት እኖራለሁ…›› ብዙ ዘይገርም የሚያስብሉ ግጥሞች ያጋጥማሉ፡፡ ጋዜጠኛ እየሩሳሌም ግርማ በኢቲቪ ሳይሆን (ወሴክማ) አዲስ
አበባ ስፖርት ፌዴሬሽን ጊቢ መረብ ኳስ ስትሰሪ ይቺን ከታች ያለችው ግጥምን ያዘለ ደብዳቤ አልደረሰሽም ነበር ይሆን? አስታውሻት፡፡
‹‹አባረህ በለው ያንን አመጸኛ ተገንጣይ ወንበዴ…
መድርሻ አሳጣው ግረፈው አሳደህ አስኪደው በዳዴ..›› የሚለውን የጥላሁንን ዜማ ግጥም
ለፍቅረኛው በጻፈው ደብዳቤ ላይ በጉልህ ያሰፈረ ልጅ አውቃለሁ፡፡ እየሩሳሌም ግርማም ታውቃለች፡፡ ያኔ ወቅቱ ስለነበር ለጉድ ስለተዜመ
እንደመረጠውም አውርቶኛል፡፡ ክስት ጥውልግ ያለ ልጅ አፍቅሮ መሆኑን ለመግለጽ…….
‹‹…ምግብ ሞልቷል አምላክ መች ነሳኝ
የፍቅር ርሃብ ነው እንዲህ ያከሳኝ…›› ቢል ያስኬዳል፡፡ ግን ፍቅር ያከሳል እንዴ? ማነው ፍቅርን ሲሪነጅ ያደረገው እና ሰውነት የሚመጠው? እዚሁ መራብ ጉዳይ ላይ እከሊት ለእከሌ ስትጽፍ ችግሬ ጭንቀቴ ምንጩ ልገባቸው
እቺ ሰው ተራበች ሲሉ
ሰማኋቸው
እኔን የራበኝ ፍቅር ነው…..›› ብላ ብትጽፍ ምኑ ይገርማል፡፡ በቃ እኔን የራበኝ
ፍርፍር ነው ብለው እንደገለበጡት ልጆች እሷም ትገልብጠው ወይስ እኔን የራበኝ…..ብላ ኦርጅናሉን ታስቀምጠው?
‹‹…እስኪ ዶሴው ይውጣ የምጠይቅበት
ወንጀሌን ሳላውቀው…›› የምትለው አንድ ሰሞን ያለጥፋት በጥርጣሬ ለታሰሩ ሁሉ ወቅታዊ
እንጉርጉሮ ሆና ነበር፡፡ እቃ የጠፋበት ‹‹ያያለ ያያለ..››ማለት ጅሮ ነበር፡፡ ‹‹..ልደው ልመደው ሆዴ…›› 1976ዓ.ም ላይ
የወጣው የኤፍሬም ታምሩ ዜማ በ1977 ዓ.ም ብቅ ላለው ድርቅ መተከዣ ሆኖ ነበር፡፡ያውም ግጥሟም ቀየር ተደርጋ
‹‹ልመደው ልመደው
ሆኔ ተወዷል ጤፍና ስንዴ
ሩዙን ብላው በዘዴ..››
ተብሏል፡፡ የሩዙ ነገር ሲነሳ አሁን በስደት እንዲህ ሆዳችን ውስጥ ሊበቅል እስኪደርስ ልንጋት..ቆዩኝማ ለካ
እኔ ራሴ ስደት ከወጣሁ በኋላ ለሚስቴ ደብዳቤ ስጽፍ ግጥም አክዬበት ነበር፡፡ ከዜማም
ከየትም ቦጨቅ የተደረች ኤደለችም፡፡ ከራሴ.
‹‹ስደት ከሄድኩበት ነጻነት ፍለጋ
ፍቅርሽን ይዤ ከትዝታሽ ስዋጋ…›› በሚል ጀመርኩ እና በሰፊው ለቀኩት፡፡ እስኪ ትዝታም
ቢሆን እናውራ…
መጣሁ….
1 Comments:
ዋው
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home