Friday, July 12, 2013

ሂጂ ነውረኛ እንዴት ሴት ልጅ ስለወሲብ ትጽፋለች?(ግሩም) ወሲብ ሴቶች ባህላችን እና ጨዋነት በኢትዮጵያ



ሂጂ ነውረኛ እንዴት ሴት ልጅ ስለወሲብ ትጽፋለች?(ግሩም)
ወሲብ ሴቶች ባህላችን እና ጨዋነት በኢትዮጵያ  
                      በተወዳጅ መኮንን
   ሴት ልጅ አታውራ ግን ትስራ ወንድ ልጅ ያውራ ይስራ የተባለ ይመስል ስለወሲብ ሴቶች ሲያነሱወግዝ ከመ አሪኦስ ማለቱ ይብቃ ሂጂ ነውረኛ ሴት ልጅ ስነሲብ እንዴት ትጽፋለች እንዳትሉ፡፡ ጉደኛ የሆነ ጽሁፍ በተወዳጅ…እስኪ ራሶትን ፈልጉት ….የት ጋር አገኙት እንወያይ…..
     አሁን እኛ ኢትዮጵያውያን ባለንበት ሁኔታ ግራ የገባኝ ነገር አለ?.....እረ ቀኝም ገብቶኛልእዚህ ጋር ወግ አጥባቂ ምናምን ከሆንክ አይምችህም አታንብበው ልበል እንዴ እንደ ጓደኞችአዬዬእባካቹ እኔ እንዲ ተብዬ ስንቱን አንብቤያለሁ መሰላችሁ!
       አንድ ወዳጄ face book ላይ ስለሴቶች ብዙ ነገር አወራና ምላሽ ልሰጠው ፈልጌ ግን ………..ቆይ ከዛ በፊት ብዙ ሊጣሩ የሚገባቸው ጉዳዬች አሉ በሚል ጠየኩ ?....ማንን እንዳትሉ ?...እራሴን:: ከራስ ማየት መቼም ምንም አይበልጥም...?????
ባደግንበት ቤተሰብአካባቢባህል……ስርዐትአገርአንድ ግራ የገባው ግልፅ ያልሆነ አካሄድ ወይም አስተምህሮ ይታየኛል:: ለኔ ነው እንግዲህ እስቲ ግልፅ ላድርገው ….ካልሆነም የሆነ ሰው ግልፅ ያደርገዋል በእርግጠኝነት።……ጥያቄው የብዙዎቻችን ነው….:: ብንወያይበት የሆነ ቦታ ላይ ትውልድ ይድንበታል…….ጥያቄዬ ግንእንደኛ ሀገር ሴቶች ብዙ ነው::እንደ አንድ ሴትም ቢሆን ብዙ ነው…???????????!
1. በባሕላችን ሴቶች ወሲብን እንዴት ነው ማወቅ ያለባቸው?
2. ጨዋነት እና ወሲብ እንዴት ይገናኛሉ በተለይ ሴቶች ላይ?
3. ድንግልና ማለት ምንድነው?...... ለአበሻ ወንድ?....ድንግል ያልሆነች ሴት ላይስ ያለው አመለካከት?
4. ወሲብን ከትዳር በፊት ስለመጀመርና ወሲብን ሳይጀምሩ ትዳር የሚይዙ ሴቶች የቱ ነው ትክክል?
5. በሀይማኖት ተቋማት ሴቶች ላይ የሚደርሰው ትፅእኖ ?
6. እውነት ወሲብ ማለት ደስታን የሚሰጥ ነገርስ ነው?.....መዝናኛ ነው?...... ትውልድ ለመተካት ነው?....... ወይስ አሳፋሪና አስነዋሪ ነው?........ ይሄስ ከሆን ፈጣሪ ተሳስትዋል ማለት ነው?........ የቱ ነው ትክክል?
ይህንን ከጠየኩ በህዋላ ወደ ራሴ ዝርዝር ስመጣ…………

     እንደቤተሰብ …..የቱ ጋር ነው በግልፅነት የተመከርነው፧?.......... ከተመከርንስ ስንቶቻችን ነን?......... ስንቶቻችን በምክሩ……. ያለምክሩም….. የሄድነው?
የሁለት መምህራን ልጅ ስሆን አንድም ቀን ስለ ወሲብ አንስተው መክረውኝ አያውቁም::……….ወደ ጓዳ ስባል ነው ያደግኩት::………ግን 5አመቴ ባልና ሚስት አውቄአለሁ.::……………..5ተኛ ክፍል ደግሞ ስለ ወሲብ አወቄአለሁ::…………15 ተኛ ክፍል የወንድ ጓደኛ ምን ማለት እንደሆነ አውቄአለሁ::……………”የፍቅር ደብዳቤ” …………”ገፋ ሲል ካልቾ” …………”ገፋ ሲል ማስፈራሪያ ሰንሰለት እየተያዘ በእረፍት ሰአት ክፍል ድረስ እየተመጣ አስፈራርተውኛል…………………………….በእድሜ በጊዜ ሂደት ሁሉንም አልፌአልሁ ……… አልዘለለኝም።…………..አላለፈኝም።…………..አላለፍኩትም ::…………በደንብ ተዳስሼ…………….. ተነክቼ…………… ነክቼ ……….::

    ግን ጥያቄዬ የመነጨው ሰሞኑን ቤቲ big Brothers Africa………….ላይ በተሰነዘሩት ሃሳቦች የተነሳ ነው ልክ አይደለችም ባለጌ ነች::!!!………… እናትዋን ሀገርዋን ቤተሰብዋን አዋርዳለች።!!!!……………………ግማሻችን ምን አገባን እንደግለሰብ መብትዋ ነው!!!!……. …………………….አትፍረድ ይፈረድብሀል !!!.. ………………ይመቻት የት ላግኛት ብሎ ለራሱ የሚያሰላስል።!.!!
ለራሴ ግን ተምታታብኝ ሁሉንም ደገፍኩ::……… ሁሉንም ተቃወምኩ ………………ግን እንደናንተ ማነው ትክክል???!!!...........የጊዜው እውነት የቱ ነው???........... ባህሉ በትክክል ይተገበራል ?........ወይስ ወሬው ይበዛል?.............ይሄ ነው እንግዲ እኔን ግራ የገባኝ……?
እኔ ምን እላለሁ መሰላቹ ………ሴቶች በዚህ ዘመን ተቸግረናል።!!! ይሄ የእኔ እውነት ነው የሌሎቻችሁን ግን እፈልገዋለው???.....
ጓደኞቼ ከምላቸው 4 ሴቶች መሀከል አይደለም ወንድ…….””……ስል ወንበርም ይሁን ወጥ……. ............”ወንድ”……. ልትል ነው ብለን የምንሮጥ እድሜያችን ከወጣትነት አልፎ ወደ ጎልማሳነት ሊቀላቅለን ያልን ሴቶች ………..ሁሉም 25አመት በላይ የሆነው…………….አትሳደቡዋ !!!. …………ቆሞ ቀር ምናምን የሚል ስድብ ሰማሁ???…..............ለምን አትሉም?............................ 1. ወንዶቹ ከጋብቻ በፊት ወሲብ ስለሚጠይቁ::………. 2. ድንግል ለሆነችው ማን ሲታገል ይውላል…….ድንግል ላልሆነችው…….ይህች የትም ስትዘል ቆይታ ……..በዚህ መሀል የድሮውን የእናቶችን ጋብቻ እየናፈቅን……….. ምንም ክፉ ደጉን ሳያውቁ ተድረው ትዳራቸው 40 እና 50 አመት የቆየላቸውን እናቶች እያሰብን……………………. ወዳጄ እንዳለው በጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ተይዘን………….በፍርሃትና…………. በፍላጎት መሀከል………ጉዳዩን ለመፈፀም ሀጥያት ነው::….. ለመተው ደግሞ እንደሰው ትዳር አማረን ::…………..ማግባት መውለድ ................ ግን ከዚህ ሁሉ ……………….እድሜያችንን በከንቱ እየፈጀነው ያለንበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው……………!!! ሃሃሃሃ
ሲቀጥል በድንግልና የሚደረገው ጋብቻ ጥቅሙና ጉዳቱ ለሴትዋ ምንድነው?

ምንም ነገር ሳያውቁ የሚያርግዙ ህፃናት ዲቃላ ወልዳ እየተባሉ ከመሰድብ ውጭ በባህላችን ከአንዳንድ ወላጆች በስተቀር ማን ይንከባከበናል?............ ወንዱስ ቢሆን ምን አይነት ችግር እንዳለበት ሳይናገር ልጃገርድ አግብቶ በቤተክርስቲያን ደንብ 5 አመታት ያለ ግንኙነት አስቀምጦ ህሊናዋን የጎዳትን እህት ባጠገቤ አለች :: የወንድ ጓደኛ ለመያዝ?..... ከተያዘስ በህዋላ የሚለውን ቀደም ብሎ ቁጭ አድርጎ በግልፅነት መንገሩ አይበጅም ወይ??...... በአሁን ሰአት ከስንት አንድ ሰው ነው ጓደኝነት ከወሲብ ለይቶ የሚያይ?............. የማይቸኩል በጓደኝነት ትውውቅ በሳምንት ግዜ ውስጥ ወሲብ ጥያቄ ይቀርባል……… እሺ ካልኩ?.............ውይ ምን አስቸኮላት?......ኤጭ…… ኤጭጭጭጭ ………..እምቢ ካልኩ………………..ምን ታካብጃለሽ …..!!! አንቺ ብቻ ነሽ እንዴ ሴት ?.......... በለው!!!!.........ሴት በባህሪዋ ደካማ ናት የሚሉ ወንዶች ስንት ናቸው? በጅምላ ሴቱ ወንዱ ብሎ ከመሰዳደብ የዘለለ ??
በአጠገቤ ካሉ ወንዶች አስሩን ጠይቄ እንደጊዜው ትዳር ለመመስረት………"በውሲብ መጣጣም የሚል መርህ የሚከተሉ" መሆናቸውን ነግረውኛል ………..ጨምረውም ...."ሳታቀምሺ ልታገቢ ነው ?"..."ምን ታካብጃለሽ???" ……………ይሄ ነገር ቡና ቁርስ ነው እንዴ ??......ብዬ ሁሉ ጠይቄ ነበር ……..ሃሃሃሃ………... አሁን እንደምንለው ሞዲፊክ ድንግልና ወይስ ቀለም ነክረን እንሂድ ለሰርግ ምስራች ከዚህ ሁሉ ትፅእኖ እንዴት አምልጦ ???.........
ልጄ እኔ ሳልመክራት ወይም ሳልነግራት በገዛሁላት ሞባይል ፌስ ቡክ ከፍታ…..” ወንድና ስስ ፌስታል አይታመንምብላ ፖስት ብታደርግ አልደነግጥም ወይ?......... 13 አመትዋ 8ተኛ ክፍል ……………በኮሌጅስ ደረጃ ቢሆን ይች ካፌ ነው ምግብዋ………. ውሎዋ ላይበረሪ ነው ……….. ግፋ ቢል ስፔስ …………በግ ተራን አታውቀው……… እየተባልን የሚደርስብን ተፅእኖ………………. ከውግቢ ውጭ አድራ አታውቅም ተብሎ የሚደርሰው ሽሙጥ………….እኮ ልጆቻችሁ ወይም እናንተ……. እኛ ………ከየቱ ነን?.....ጨዋነት የቱ ነው ?.......ተደብቆ ስር መስደድ ?...ውይስ ሳያውቁ መጎዳት?...... ነገሩን ቀለል አድርጎ እንደ ቤቲ ሳያካብዱ ……………ሃሃሃሃ !!!……በአለም መታየት ??........ብቻ ጥያቄዬ ይሄ ሁሉ ነው ?………..የቤቲስ ስራ ከየቱ ነው ?........ የትኛው ተፅእኖ ነው ?.......ለስዋ ልክ እናትዋ አስተምረው ወይም መክረዋት ይሆን ??.... ወይስ?........... ልጅትዋ ግራ ከመጋባትዋ የተነሳ ለጋዜጠኛ የምትመልሳቸው መልሶች በራስ የመትማመን ይሁን…… ግራ የመጋባት…… የማያስረዳ…………. እናቴ ያደረግችውን ቃለ መጠይቅ ሰምቼዋለሁ :: ደግሞ…… የሌሎቹን ሰዎች አልሰማሁትም ……ውይ ስታሳዝን ግራ ገባት እኮ::…. እንደ ጓደኞችዋ ጎብዝ ልበ ሙሉ ::….እንደ እናትዋ ደግሞ አንገት ደፊ።…….ግራ መጋባት ይሉሃል ይሄኔ ነው……..!! ሃሃሃሃ
በጣም የገረመኝ የህግ ባለሙያዎች ተደራጅተው አደራጅተው ህጉን አጣርተው ሊከስዋት መነሳታቸውን ስሰማ ህጉም ተግባራዊነቱም ፍትሁም ናፈቀኝ ::…..የአስር አመት ህፃናት ወንዶች በየትምህርት ቤቱ እየተደፈሩ………. የስድስት ወር እና የአንድ አመት ጨቅላ ሴቶች እየተደፈሩ …………እነሱን መታደግ ትቶ ይቺን ትልቅ ሴት ሊያውም ፈልጋ አስባበት ያደርገችውን ለመክሰስ መጣጣር ምን ይሉታል ብዬ በደካማ አስተሳሰቤ ተገርሜአለሁ ::………..እስቲ እዚህ ጋር ማነህ በቀደም ጠበቃ ነኝ ያልከው………………ሃሃሃሃ
ፅሁፌን ግን ሳጠቃልል በሴቶች ዙሪያ እንደ ባህል…… እንደ ሀገር …….እንደ አስትዳደግ ………የምናነሳ ከሆነ ብዙ ባህሎችታሪኮች….. የእምነት ትምህርቶች ……..እውነታውበአሁን ሰአት በጣም ይጣረሳል::!!!! “……የሰው ፍላጎት ልክ እንደጊዜው እንደሰው በጣም ይቀያየራል። ስለዚህ ለወደፊት ከቻልን………………. አሁን ዙሪያችን ላሉ ታናናሾቻችን እውነታውን ከጉዳት በፊት አስተውለው እንዲያደርጉት ከአሁኑ መምከር እንዴት እንችላለን ? ትውልድ ከባህሉ ከጊዜው ጋር መሄድ ይችላል ?የወንድ ጓደኛ ለመያዝ ከተያዘስ ከዛ በህዋላ የሚለውን ቀደም ብሎ ቁጭ አድርጎ በግልፅነት መንገሩ አይበጅም ወይ ? እዚህ ጋር ስለ ቤቲ ብዙ ያላችሁ ጓደኞቼን ታግ ማድረግ ፈልጌ ነበር ግን ሳላስፈቅድ በሚለው ትቼዋለሁ:: ግን ሃሳባቹን ስጡኝ እባካቹ????......በእነዚህና ከእነዚህም በላይ በሆኑ ተፅእኖዎች ጀርባ እኛ ሴቶች ከወዴት እንሁን ????..........እስቲ የደገፋችሁም የተቃወማችሁም አስተያየት ስጡ?? Cheers!!

0 Comments:

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home