ቡሄ እና ትዝታው
በግሩም ተ/ሀይማኖት
አንዳንዴ ትዝታ በትዝታ ማህደር ውስጥ እንዳዳፈኑት እሳት ተዳፍኖ እንዳይቀመጥ የሚቀሰቅስ አይጠፋም፡፡ የቡሄ ትታዬን ልከትበው ባላስብም
የወዳጄ ፋሲል ተካልኝን ጽሁፍ ሳይ የተዳፈነው አልዳፈንም ብሎ አደባባይ ሊወጣ መጣ፡፡ የመጣውን ጻፍኩት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ
ፋሲል ‹‹..ስደትን በማባባስ..ዋና ተጠያቂው መንግሥት ቢሆንም..ጠንሳሾቹና አነሳሾቹ ግን...ቡሄ ጨፋሪዎች ይመስሉኛል::...(አቅም እንደሌላቸው
ስለማውቅ ነው - ተጠያቂ ያደረግኩዋቸው:: ማንም በአቅመ-ቢሱ ላይ
ይበረታል አይደል?!?...)ለማንኛውም ቡሄ ጨፋሪዎቹ :-
"...እዛ ማዶ አንድ ኮንጐ..
እዚ ማዶ አንድ ኮንጐ..
የኔማ እንትና..ሊሔድ ነው ቶጐ::"
...እያሉ::……….›› ብሎ ያሰፈረውን ሳይ የቡሄ ጭፈራ እንዲህ ቅጡን ሳያጣ አንዴ በልጅነቴ ጨፍሬ ነበር፡፡ ዛሬ ነበር ላይ ሆኜ እቆዝማለሁ፡፡ ምን እኔ ብቻ..እናንተም ጭምር ሆነን እንቆዝማለን፡፡ ሴቶችም አበባየሆሽ አልፎባችሁ ነበር ላይ የትዝታ ማህደራችሁን የከፈታችሁ አንድ ሆነናል አይዟችሁ፡፡ …ታዲያ መለስ ብዬ የትዝታ ማህደሬን ስቃኘው አንዴ ብቻ የጨፈርኩበት የቡሄ ትዝታ ሌላ ጊዜ ተመልካች አድርጉኝ ጥሎብኝ ያለፈውን ጉልህ ታሪክ እንሆ፡-
ይበረታል አይደል?!?...)ለማንኛውም ቡሄ ጨፋሪዎቹ :-
"...እዛ ማዶ አንድ ኮንጐ..
እዚ ማዶ አንድ ኮንጐ..
የኔማ እንትና..ሊሔድ ነው ቶጐ::"
...እያሉ::……….›› ብሎ ያሰፈረውን ሳይ የቡሄ ጭፈራ እንዲህ ቅጡን ሳያጣ አንዴ በልጅነቴ ጨፍሬ ነበር፡፡ ዛሬ ነበር ላይ ሆኜ እቆዝማለሁ፡፡ ምን እኔ ብቻ..እናንተም ጭምር ሆነን እንቆዝማለን፡፡ ሴቶችም አበባየሆሽ አልፎባችሁ ነበር ላይ የትዝታ ማህደራችሁን የከፈታችሁ አንድ ሆነናል አይዟችሁ፡፡ …ታዲያ መለስ ብዬ የትዝታ ማህደሬን ስቃኘው አንዴ ብቻ የጨፈርኩበት የቡሄ ትዝታ ሌላ ጊዜ ተመልካች አድርጉኝ ጥሎብኝ ያለፈውን ጉልህ ታሪክ እንሆ፡-
አሁን ማን
የሙት በልጅነት ዘመንህ አንዴ ብቻ ነው ሆያ ሖዬ ያልከው ትሉኝ ይሆናል…ይሁን በሉኝ፡፡ ግን እናቴ ከነበራት ጥላቻ አንጻር እኔም
ሆንኩ እህቴ ለቡሄም ሆነ ለእንቁጣጣሽ..አይፈቀድልንም፡፡ እህቴ ከነአካቴው አበባየሆሽ ያለች አይመሰለኝም፡፡ እናቴ እንዳልጨፍር
ከምትሰጠኝ ምክንያት ውስጥ ድሮ ለበአሉ ነበር ጭፈራው አሁን ለገንዘብ ነው፡፡ ልመና ደግሞ ለእኛ ቤት አልተፈቀደልንም፡፡ እድልም
የለንም፡፡…የመሳሰለ ብዙ ምክንያት ትደረድራለች….ደጉ ዘመን ነገር የማያንሸዋርሩበት ጊዜ ሆኖ ነው እንጂ ልመና ለእኛ ቤት አልተፈቀደም..ስትል
ለሌላው ተፈቅዷል ወይ ብለው ጸብ ያለሽ በዳቦ….(ኤጭ!!!!...ዛሬ እንኳን እስኪ ጸብ ያለሽ በሙልሙል እንበል…ቡሄ አይደለ?)
በቃ!..ሁሌ ቡሄ አትጨፍር ስባል በጉጉት ተወጥሬ እከተላቸው እና በርቀት ሲጨፍሩ አያለሁ፡፡ አንዴ ነሸጥ አደረገኝ እና እኔም አለሁብት
ብዬ ስጨፍር ዋልኩ፡፡ ወንደሰን ሰብስቤ…ነብዩ ሀይሉ…ዳንኤል መሀሪ…ሌላ ማን ነበር? አስታውሱኝ እስኪ..ቅድስተ ማርያም ነን ያላችሁ
እስኪ እንያችሁ…..እያልኩ ነው፡፡ እኔን ዲቪ ይርሳኝ…ዘውዱ አዲስ በዲቪ አሜሪካን ሲከትም ጊዜ ዘነጋሁት…ዱላችንን ይዘን ከቤት
ቤት እየዞርን እንጨፍራለን፡፡
ሀይሌ ሩት‹‹..እርጅና ጣና ድቅን አለ ፊቴ…›› እንዳለው ‹‹ጉርምስና
መጣና ውፍር አለ ድምጼ..›› ሳልል በፊት ስለነበር ያኔ በጥሩ ድምጽ ጨፈርኩ፡፡ ‹‹..ሆያ ሆዬ…ሆሆሆ..›› ዱላው እግም..እግም…ቆርኪ
ቀጥቅጠን በስተን በሽቦ አስረን ያዘጋጀነው እንደ ጽናጽል የሚንሸዋሸው….ክሽክሽም እንደዛው ይንከሻከሻል፡፡ ክፈት በለው በሩን የጌታዬን…ክፈት
በለው ተነሳ ያንን አንበሳ…ሰፈራችን ላሉ ጥቂት ጊቢ ያላቸው ቤቶች የሚባል ነው፡፡ ሌላው ልሙጥ በረነዳ የናፈቀው መንደር ስለሆነ
ቀጥታ ሄዶ ሆያ ሆዮ በማለት ይጀመራል…..ይጨፈራል፡፡ አሁን ወዳጄ ፋሲል እንዳለውም
"..እዛ ማዶ አንድ ሲሳይ..
እዚ ማዶ ሌላ ሲሳይ..
የእከሌ ልጅ..ሔደ ፈረንሳይ::›› አይነት ቅጥ ያጡ ግጥሞች ዛሬ ሳይሆን መሰግሰግ የጀመሩት በእኛ ጊዜም ነው፡፡
እዚ ማዶ ሌላ ሲሳይ..
የእከሌ ልጅ..ሔደ ፈረንሳይ::›› አይነት ቅጥ ያጡ ግጥሞች ዛሬ ሳይሆን መሰግሰግ የጀመሩት በእኛ ጊዜም ነው፡፡
እዛ
ማዶ በረኪና…እዚህ ማዶ በረኪና
የኔማ
እንትና….ባለ መኪና..እያለ ይወርዳል፡፡ እናቴም ይሄን ጠልታ ይሆናል እንዳንጨፍር የምትከለክለን፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ተደብቄ
ጨፈርኩ እና የተሰጠንን ሙልሙል ሸጠን ሳንቲሙን ተካፈልን፡፡ ረስቼው ሳንቲሙን ሳልደብቅ ገባሁ፡፡
ተገኘብኝ…
አቤት
የተገረፍኩት.. አቤት ቁንጥጫው…. በርበሬ ታጠንኩኝ፡፡ ከዛ በኋላ ሆያ ሆዬ የሚለውን ስሰማ ያ-ጣር ያ-ዱላ የታጠንኩት በርበሬ
ነው ትዝ የሚለኝ፡፡…..በዘፈን ስሰማ እንኳን መሸሽ ነው የሚያምረኝ…….ዛሬ ግን በትዝታ የተቋጠረ ሲጨፍሩ ማየት እንኳን
የማልችለው ሆኖብኛል፡፡ አይ ቡሄ እንደዛ አስገርፎኝ እስከዛሬ አለ……
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home